Customs Proclamation No.859-2014
20th Year No. 82 ADDIS ABABA 9th December, 2014
Filed under: Legislation, Tax and customs

Customs Proclamation No.859-2014
20th Year No. 82 ADDIS ABABA 9th December, 2014
Ethiopian city bans smoking in public places | Capital News.
Source: CAPITAL NEWS
Ethiopia, Jan 13 – An Ethiopian city has banned smoking in public places with fines more than an average monthly wage, the first city in the country to do so, reports said Tuesday.
The decision by the northeastern city of Mekele, capital of the Tigray region, makes smoking illegal in bars, restaurants, schools and hospitals, as well as outdoors in stadiums and during religious festivals.
Advertising tobacco is also banned, Ethiopian media reported.
Fines have been set at $50 for individuals and $150 for owners of bars or restaurants, a stiff punishment in a country where average monthly salaries are less than $40, according to the World Bank.
Ethiopia’s parliament last year voted to ban smoking in public places to combat tobacco-related diseases, but the law had not been enforced until now.
Nearly one in 10 young Ethiopians smoke, according to the World Health Organization.
ብዙዎቻችሁ የEthiopian Legal Brief ጎብኚዎች wordpress.com ላይ በላልበልሃ የሚል ብሎግ እንዳለኝ የምታውቁ ይመስለኛል፡፡ ሆኖም ከስራ ብዛትና በቀላሉ ኢንተርኔት ከማግኘት ችግር የተነሳ ከጊዜ ወዲህ በላልበልሃ ላይ ብሎግ ማድረግ አቁሜያለው፡፡ በቅርቡም ለብሎጉ ጎብኚዎችና subscribers በይፋ በማሳወቅ ብሎጉን delete ለማድረግ አስቤያለው፡፡ ጽሁፎቹን ያላነበቡና በድጋሚ ለማንበብ የሚፈልጉ እንደሚኖሩ በመረዳት የተወሰኑትን Ethiopian Legal Brief ላይ አወጣቸዋለው፡፡
የሚከተሉት የችሎት ገጠመኞችና ቀልዶች ከፊሎቹ በላልበልሃ ላይ የወጡ ሲሆን የተቀሩት አዲስ ናቸው፡፡ የህግ ሰዎች! እስቲ ትንሽ ዘና እንበል፡፡
የችሎት ገጠመኞች
ቅርንጫፍ የሌለው ባንክ
ምስክሩ የምስክርነት ቃሉን በእውነት ለመስጠት ቃለ-መሃላ ፈጽሞ ከዳኛው ፊት ለፊት ተቀመጠ፡፡ ዳኛውም ስም ዕድሜ አድራሻ ከጠየቁት በኋላ ቀጣዩን ጥያቄ አቀረቡለት፡፡
ስራ?
ምስክር – ባንክ
ዳኛ – የትኛው ባንክ?
ምስክር – አይ አይደለም ጌታዬ! እኔ እቺ የቆርቆሮ ባንክ ነው የምሰራው፡፡
ቻርጅ እና ቻርጀር
በሞባይል ስልክ ስርቆት ተጠርጥሮ ክስ የቀረበበት አንድ ግለሰብ በቀጠሮው ቀን ፍርድ ቤት ሲቀርብ ዳኛው ‹‹ቻርጁ ደርሶሃል?›› ሲሉ ይጠይቁታል፡፡ ምን ያለበት ምን አይችልም እንዲሉ የዳኛውን ጥያቄ በወጉ ያልተረዳው ተከሳሽ “የምን ቻርጀር?” እኔ የወሰድኩት ሞባይል ብቻ ነው” በማለት ፈጣን ቃሉን ሰጥቷል፡፡
መከላከያ በችሎት
በአንድ ወቅት በወንጀል የተፈረደበት አንድ ደንበኛ ይግባኝ እንዳቀርብለት ጠይቆኝ ስለጉዳዩ የበለጠ ለመረዳት አንዳንድ ጥያቄዎች አቀረብኩለት፡፡ ትንሽ ማውራት እንጀመርን የተከሰሰበትን ድርጊት በበቂ ሁኔታ የሚያስተባብሉ የሰነድና የሰው ማስረጃ እንዳሉት ተረዳሁ፡፡ ይሁን እንጂ ፍርዱን ሳነበው ተከላከል የሚል ብይን ከተሰጠበት በኋላ መከላከያ እንዳለው ሲጠየቅ “የለኝም” ብሏል::
እኔም ይህ ሁሉ በቂ ማስረጃ እያለው ለምን መከላከያውን እንዳላቀረበ በጣም ተገርሜ መከላከያ እንዲያቀርብ ዕድል የተሰጠው መሆኑን ጠየቅኩት፡፡
እሱም “አዎ መከላከያ አለህ? ሲለኝ የለኝም” ብያለው
የባሰ በመገረም “ለምን?” ብዬ ጠየቅኩት::
“መከላከያ ሲል መከላከያ ሰራዊት መሰለኛ!”
የችሎት ቀልዶች
ተከሳሽ– “ክቡር ፍርድ ቤት ሌላ ተከላካይ ጠበቃ እንዲሾምልኝ እጠይቃለሁ::”
ዳኛ– “ምንድነው ምክንያትህ?”
ተከሳሽ– “ይሄኛው ተከላካይ ጠበቃ የኔን ጉዳይ ችላ ብሎታል፡፡
ዳኛ– ወደ ተከላካይ ጠበቃ ዞረው “እህ ለተከሳሹ ቅሬታ የምትለው ነገር አለህ?”
ተከላካይ ጠበቃ– “ኧ!? ምን አሉኝ? ይቅርታ ጌታዬ እየሰማሁ አልነበረም፡፡”
* * * * * * * * * *
ዳኛው ተከሳሹን “ፍርድ ቤት ተከላካይ ጠበቃ እንዲያቆምልህ ትፈልጋለህ?” ሲሉ ይጠይቁታል
ተከሳሽ –“አይ በራሴ ብከራከር እመርጣለሁ፡፡ የቀረበበኝ ክስ እኮ በጣም ከባድ ነው!”
* * * * * * * * * *
በአንድ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ክስ ዐቃቤ ህጉ ዳኛውን “ጌታዬ ይህ ድርጊት የተፈጸመው ተስተናጋጅ ጢም ብሎ በሞላበት ሬስቶራንት ውስጥ ነው፡፡” ብሎ መናገር ሲጀምር በነገሩ የተደመሙት ዳኛ “በእኔ ተሞክሮ ግን ይህን መሰል ድርጊቶች የሚፈጸሙት ተስተናጋጅ በሌለበትና ሬስቶራንቱ ዝግ በሚሆንበት ጊዜ ነው፡፡” ሲሉት ዐቃቤ ህጉ ነገረኛ ቢጤ ነበረና “አይ ጌታዬ! እኔ እንኳን እንደዛ ዐይነት ተሞክሮ የለኝም!” በማለት የተከበሩት ዳኛ ላይ አላግጦባቸዋል፡፡
* * * * * * * * * *
ዳኛው የተምታታ ክርክር እያቀረበ ሃሳቡ አልጨበጥ ያላቸውን ጠበቃ “ያንተን ክርክር ጭራውን እንኳን ለመያዝ አቅቶኛል፡፡ በአንዱ ጆሮ ገብቶ በሌላኛው ይወጣል” ይሉታል፡፡ ጠበቃውም የሚሸነፍ ዓይነት አልነበረምና “ጌታዬ በመሀል ሆኖ የሚያቆመው ነገር ምን አለ?” ሲል መልሶላቸዋል፡፡
* * * * * * * * * *
ከግራ ወደቀኝ እየተመላለሰ ባለማቋረጥ ለረጅም ጊዜ ክርክሩን በማቅረብ ላይ ያለ አንድ ሞቅ ያለው ጠበቃ በንግግሩ መሀል ቆም ብሎ “እየተከተሉኝ ነው ጌታዬ?” ሲል ዳኛውን ይጠይቃቸዋል፡፡ ዳኛውም “አዎ በቅርበት እተከተልኩህ ነው፡፡ ግን ግራ የገባኝ ነገር ወዴት ነው የምትሄደው?” በማለት መልሰው በነገር ጠቅ አድርገውታል፡፡
(ይህ ጽሁፍ ከዓመታት በፊት ማክዳ በምትባል መጽሔት ወጥቶ የነበረ ሲሆን አሁን ካለው ህግ አንጻር ተቃኝቶ በድጋሚ ቀርቧል፡፡)
ከዓመታት በፊት በአገራችን ሳምንታዊ የግል ጋዜጣ ላይ እንዲህ የሚል ማስታወቂያ ወጥቶ አይቻለሁ ‹‹እባካችሁ እርዱኝ አንዱ ኩላሊታችሁን ለግሱኝ›› የለግሱኝ ጥሪው ህይወት ማዳን እስከሆነ ድረስ ማስታወቂያው በተለየ መልኩ አትኩሮታችንን ላይስብ ይችላል፡፡ ግን ማስታወቂያው በስተመጨረሻው ላይ ማጠቃለያ መልዕክትም አለው፡፡ ‹‹ኩላሊቱን ለግሶ ህይወቴን ላዳነልኝ ግለሰብ ወሮታውን እከፍላለሁ፡፡›› የክፍያው መጠን ባይገለጽም በማስታወቂያው ላይ የቀረበው ጥያቄ ‹ነፃ› ወይም ‹ልግስና› ስላለመሆኑ ድምዳሜ ላይ መድረስ አይከብድም፡፡ ልግስናም ተባለ ሌላ ስያሜ ተሰጠው ለሚሰጠው ነገር በልዋጩ የሚከፈል ዋጋ እስካለ ድረስ የውሉ ዓይነት ከስጦታ ውል ወደ ሽያጭ ውል ይሸጋገራል፡፡
አሁን ላይ ቢሆን ኖሮ ይህን መሰሉ ማስታወቂያ በህግ የተከለከለ በመሆኑ የጋዜጣው ባለቤትም ደፍሮ አያወጣውም፡፡ በማስታወቂያ አዋጅ ቁጥር 759/2009 በአንቀጽ 6(1)(ሀ) እንደተመለከተው የማንኛውም ማስታወቂያ ይዘት ህግና ስነ-ምግባርን የማይጻረር መሆን አለበት፡፡ አዋጁ በአንቀጽ 7 ላይ ህግና ስነ-ምግባርን የሚጻረሩ በማለት ከፈረጃቸው የማስታወቂያ ይዘቶች አንዱ የሕብረተሰቡን አካላዊና አእምሯዊ ጤንነት ወይም ደህንነት ለጉዳት የሚያጋልጥ ድርጊት እንዲፈጸም የሚያነሳሳ ማስታወቂያ ነው፡፡ ስለሆነም ማስታወቂያው ከዚህ ውስጥ የሚመደብ እንደመሆኑ ክልከላ ተደርጎበታል፡፡ ክልከላውን መተላለፍ የወንጀል ድርጊት ሲሆን ከብር 20ሺ በማያንስና ከብር 150ሺ በማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ ያስቀጣል፡፡ [የማስታወቂያ አዋጅ ቁጥር 759/2009 አንቀጽ 34(1)(ሐ)]
ትኩረቴ በማስታወቂያ አዋጁ ላይ ሳይሆን ከሰውነት አካል ሽያጭ በተለይም ከኩላሊት ሽያጭ ጋር በተያያዘ የህግና የስነ-ምግባር ጉዳዮችን መዳሰስ ይሆናል፡፡ ኩላሊታችንን ብንሸጠውስ? ምን ችግር አለው?
ኩላሊትን ጨምሮ የሌሎች የሰውነት አካላት ሽያጭ ከህግና ከሥነ-ምግባር አንፃር ያስከትሉት ውዝግብና ንትርክ በአሁኑ ወቅት ጡዘት ላይ የደረሰ ቢሆንም ድርጊቱ ከተጀመረና ከተጧጧፈ ግን ከ20 ዓመት በላይ ሆኖታል፡፡ በተለይ የኩላሊት ሽያጭ ሻጩ ከመሞቱ በፊት የሚደረግ ግብይት በመሆኑና ወሰን ሳይገድበው በየአህጉሩ በፍጥነት እየተስፋፋ በመሆኑ የየአገሪቱ የህክምና ባለሙያዎች፤ የፓርላማ አባላትና ሌሎች በጉዳዩ ያገባናል የሚሉ ደጋፊና ተቃዋሚ ወገኖች ግራ ቀኝ ይዘው ክርክራቸውን እየጧጧፉት ነው፡፡
የኩላሊት ገበያውም ከቀን ወደ ቀን እየደራ ኩላሊትም እየተቸበቸበ ይገኛል፡፡ በህንድ፣ በደቡብ አሜሪካ፣ በሩሲያ፣ በአውሮፓና በአረብ አገራት ኩላሊት ከሰውነት የአካል ክፍልነት ወደ ሸቀጥነት እየተቀየረ የመምጣቱ ሁኔታ ድርጊቱ ስር የሚሰድና ወደፊትም መግቻ ቁልፍ ለማግኘት አዳጋች የሚያደርገው ይመስላል፡፡ በተለይ አንዲት የህንድ መንደር ከሞላ ጎደል ሁሉም ነዋሪዎቿ አንድ ኩላሊታቸውን ሸጠው በአንዱ ብቻ የሚኖሩበት በመሆኑ ‹የኩላሊት ቀጠና› (kidney district) የሚል ስያሜ ልታገኝ ችላለች፡፡
የህጉን አቋም ስንመለከት በብዙ አገሮች የሰውነት ክፍሎችን መሸጥ ሆነ መግዛት በግልጽ የተከለከለ ነው፡፡ በአገራችን አሁን ባለው የወንጀል ህግ መሰረት ገንዘብ አሊያም ጥቅም ለማግኘት ብሎ የሰውነት አካልን መስጠት ሆነ በተጎጂው ፈቃድ መውሰድ ሁለቱም በወንጀል ያስቀጣሉ፡፡ በወንጀል ህጉ አንቀጽ 573(1) እንደተመለከተው ገንዘብ አሊያም ጥቅም ለማግኘት ብሎ የሰውነት አካልን መስጠት እንዲሁም ከሞት በኋላ የሰውነት ክፍልን ለሌላ ሰው ወይም ድርጅት ለማስተላለፍ መስማማት በቀላል እስራት ወይም በመቀጮ ያስቀጣል፡፡
ቅጣቱ በሰጪ ላይ ቀላል ሲሆን በተቀባዩ ላይ ግን ህጉ የሚያስቀምጠው ቅጣት ከበደ ያለ ነው፡፡ በዚሁ መሰረት ገንዘብ አሊያም ጥቅም ለማግኘት በተበዳዩ ፍቃድ የሰውነት አካልን መውሰድ ተጎጂው እያለ ከሆነ ከአምስት ዓመት እስከ አስር ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት የሚያስቀጣ ሲሆን ከተበዳዩ ሞት በኋላ ከሆነ ደግሞ ከአምስት አመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት ያስቀጣል፡፡ [የወንጀል ህግ ቁጥር 573(2)]
በተመሳሳይ መልኩ በፍትሕብሔር ህግ ቁጥር 18 ላይ እንደተመለከተው ሙሉ አካልነትን /integrity of the body/ የሚያቃውስ ማንኛውም የሰውነት ክፍሎች ላይ የሚፈፀም ተግባር የተከለከለ ነውው፡ በሌላ አነጋገር አንዲት ሴት ፀጉሯን ቆርጣ ብትሸጥ ወይም ደም ብትለግስ ፀጉሩም ጊዜውን ጠብቆ ስለሚያድግና ደሙም ከ48 ሰዓታት በኋላ ስለሚተካ ሙሉ አካልነትን የሚያቃውስ ተግባር ባለመሆኑ የተፈቀደ ነው፡፡ ከሁለት ኩላሊቶች መካከል አንደኛው ተቆርጦ ቢወጣ ግን ምንም እንኳን ከባድ የሚባል የጤና ቀውስ ባያስከትልም አንድ ሰው በተፈጥሮ ሊኖረው የሚገባውን አካላዊ መዋቅር የሚቃረን በመሆኑ የሽያጭ ድርጊቱም በአንቀጽ 18 መሰረት የተከለከለ ነው፡፡ በውል ህጋችን አንቀጽ 1678 (ለ) እና 1716(ሀ) መሰረት አንድ ውል ህጋዊ ውጤት እንዲኖረው የውለታው ጉዳይ ህጋዊና ሥነ-ምግባርን የማይቃረን መሆን እንዳለበት በመደንገጉ በኩላሊት ሻጭና ገዢ መካከል የሚደረገው ውል ዋጋ አልባ እንደሆነ ይቀራል፡፡
በፍትሐብሔር ህጉ በጥቅል ከተቀመጠው በተጨማሪ የአካላት ክፍሎችና ህብረ-ሕዋሳት ልገሳና ሽያጭ በተመለከተ ቁጥጥር የሚያደርግ ህግ እስካሁን በቀጥታ በህግ አውጪው የወጣ ባይሆንም የምግብ፤ የመድሃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 661/2001ን ለማስፈጸም የወጣው የምግብ፤ የመድሃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 299/2006 ይህን ጉዳይ አስመልክቶ ዝርዝር ድንጋጌዎችን ይዟል፡፡ በዚሁ መሰረት በደንቡ አንቀጽ 59 ንዑስ አንቀጽ 2 እንደተመለከተው አንድ ሰው በህይወት ዘመኑ ወይም ህይወቱ ካለፈ በኋላ የአካል ክፍሎቹንና ህብረ-ህዋሳቱን በልገሳ ለማስተላለፍ ሆነ በምንም መልኩ እንዳይወሰዱ ለመከልከል ያልተገደበ ነጻነት ተሰጥቶታል፡፡
ይህም ማለት የአካል ክፍሎችንና ህብረ-ህዋሳትን በሕይወት ዘመን ወይም ከሞት በኋላ ለሌላ ሰው ወይም ድርጅት በሽያጭ ማስተላለፍ ሆነ ለማስተላለፍ መስማማት ክልከላ የተደረገበት [ደንብ ቁጥር 299/2006 አንቀጽ 59 ንዑስ አንቀጽ 5] ቢሆንም ያለምንም ወሮታ ሆነ ክፍያ ከሆነ ግን “እሰጣለው” የሚለው የተስፋ ቃል በህግ ተቀባይነት ተሰጥቶታል፡፡ የአካል ክፍሎችንና ህብረ-ህዋሳትን ለመለገስ የሚሰጠው የተስፋ ቃል ተስፋ ሰጪው በህይወት ባለበት በማንኛውም ጊዜ ሊሽረው መብት አለው፡፡ የመሻሩ ውጤት ለጋሹ ከግዴታ ነጻ የሚያደርገው ሲሆን ተለጋሹ በተሰጠው የተስፋ ቃል ተነሳሰስቶ ላደረገው ወጪ ሁሉ (በተለይ የተስፋ ቃሉ በክፉ ልቦና የተሰጠ ከሆነ) ለጋሹ ካሳ የመክፈል ግዴታ ተጥሎበታል፡፡ [ደንብ ቁጥር 299/2006 አንቀጽ 59 ንዑስ አንቀጽ 3 እና 4]
አንድ ሰው ህጋዊ በሆነ የተስፋ ቃል የአካል ክፍሎችን ወይም ህብረ-ህዋሳትን ከሌላ ሰው ማግኘቱ በራሱ ሰውነት ላይ ወዲያኑ በህክምና ንቅለ-ተከላ (transplantation) ሊደረግለት ይችላል ማለት አይደለም፡፡ ደንብ ቁጥር 299/2006 አንቀጽ 59 ንዑስ አንቀጽ 1 ላይ እንተመለከተው የአካል ክፍሎችና ህብረ-ህዋሳት ንቅለ-ተከላ ማከናወን የሚቻለው የተቀባዩን ህይወት ለማቆየት ወይም የሰውነት አቋሙን ለማስተካከል ሌላ የተሻለ አማራጭ መንገድ የማይገኝ መሆኑ በሕክምና ቦርድ ሲረጋገጥ ነው፡፡
በሌሎች ብዙ አገራት የኩላሊት ሽያጭ በህግ የተከለከለ ተግባር ሲሆን በተወሰኑት ደግሞ በወንጀል ጭምር የሚያስቀጣ ድርጊት ነው፡፡ አሁንም ቢሆን ግን በሁለት ጎራዎች መሃል ለሙግትና ክርክር መንስዔ የሚሆነው ጥያቄ እየተነሳ የጦፈ ክርክር እየተደረገበት ይገኛል፡፡ ኩላሊት በህጋዊ መንገድ መሸጥ አለበት ወይስ የለበትም? ከወደ እንግሊዝና ህንድ አካባቢ ለዚህ ጥያቄ የሚሰጡት መልሶች በየራሳቸው ጠንካራ እና ሚዛን የሚደፉ ናቸው፡፡ የኩላሊት ሽያጭን የሚደግፉ ወገኖች ድርጊቱ የሁለትዮሽ ጠቀሜታ እንዳለው ይገልፃሉ፡፡ ‹‹በአንድ በኩል በኩላሊት እጦት ሊሞት የነበረው ግለሰብ ከሞት ይተርፋል፡፡ በሌላ በኩል በከፋ ድህነት ውስጥ ሲማቅቅ የነበረው ግለሰብ ጤናው ሳይቃወስ አንደኛው ኩላሊቱን በመሸጥ ከድህነት ቀንበር በቀላሉ ይቀቃል›› ይህን ይመስላል የሚያቀርቡት ሃሳብ፡፡ ከዚህ ሃሳባቸው ተነስተው የሚደርሱበት ድምዳሜም ድርጊቱ ሥነ-ምግባርን የማይፃረር እግዜርም የሚወደው ስራ እንደሆነ ነው፡፡ የአንድ ኩላሊት የገበያ ዋጋ እስከ እስከ አምስት ሺ ዶላርና ከዛም በላይ የሚደርስ ሲሆን በእርግጥም ይህ ገንዘብ የደሃን ህይወት በከፊል ሊቀይር ይችላል፡፡
ከዚህ ሃሳብ በተቃራኒ የተሰለፉት ወገኖች ከሰው ልጅ ሰብዓዊ ክብር አንፃር ለገንዘብ ብሎ የተከበረውን የሰው ልጅ የሰውነት አካል መሸጥ አስነዋሪነቱን በማስረገጥ ድርጊቱን አምርረው ይቃወማሉ፡፡ ደጋፊዎች ባይጠፉም በርካታ ሐኪሞችም ድርጊቱ በህክምና ሥነ-ምግባር ተቀባይነት እንደሌለው በመግለጽ ተቃውሞአቸውን አሰምተዋል፡፡ ከተቃዋሚዎች ጎራ ክፉኛ ነቀፌታ የገጠመው ኩላሊት በገንዘብ ይሸጥ መባሉ ብቻ ነው፡፡ እስከ አሁን ድረስ በፈቃደኝነት የተመሰረተ ነፃ የኩላሊት ልገሳ ወይም ስጦታ ውግዘት አልገጠመውም፡፡ ሽያጩን ግን ‹‹የሰው ልጅን ክብር የሚያቆሽሽ›› በሚል ነው የሚገልጹት፡፡ የአገራችን ህግም ቢሆን የሰው ህይወትን ለማዳን ኩላሊትን ሆነ ሌላ የሰውነት አካልን በነጻ መስጠት ወይም መለገስ በወንጀልነት አይፈርጀውም፡፡
ሌላው ተደጋግሞ የሚሰማው ስሞታ ከኩላሊት ሽያጭ የሚገኘው ገንዘብ በአግባቡ ለባለኩላሊቶች አለመድረሱና ህይወታቸውንም አለመለወጡ ነው፡፡ የኩላሊት ሽያጭ ከተፈቀደ ‹‹የኩላሊት ዘረፋ ወንጀል›› በእጅጉ እንደሚባባስ ስጋታቸውን የገለፁም አልጠፉም፡፡ ይሁን እንጂ አፈፃፀሙና አተገባበሩ በመንግስት ቁጥጥር ስር በሚሆን የገበያ ስርዓት ህጋዊ መንገድ መዘርጋት ሊፈጠር ለሚችለው ስጋትና ችግር ፍቱን መፍትሄ እንደሆነ በመግለጽ የኩላሊት ሽያጭ ደጋፊዎች ችግሩን ያጣጥሉታል፡፡ ወንጀሉ በዚሁ መልኩ የሚወገድ አለመሆኑን በመጥቀስም ህጋዊነት ብቸኛው መፍትሄ እንደሆነ ለማሳመን ይጥራሉ፡፡ የኩላሊት ሽያጭ ደጋፊዎች በሽያጩ ሂደት ከባለኩላሊቱ ይልቅ በመሃል የሚንሳፈፉ ሶስተኛ ወገን ደላሎች ይበልጥ ተጠቃሚዎች እንዳይሆኑ የሚቀርበውን ስጋት በተመሳሳይ መልኩ ህጋዊ የመቆጣጠሪያ ስልት በመቀየስና አፈፃፀሙን በበላይነት የሚመሩ ድርጅቶችን በማቋቋም ግንኙነቱ በሻጭና በገዢ መካከል ብቻ እንዲሆን በማድረግ ውጤታማ በሆነ መንገድ ሊካሄድ እንደሚችል ለማሳመን ይጥራሉ፡፡
ሌላው በተጠቃሚዎች የሚሰነዘረው ሂስ ሽያጩ የኩላሊት ልገሳ ወይም ነፃና ሰብዓዊ እርዳታን መሰረት ያደረገ የኩላሊት ስጦታን ያዳክማል የሚል ሲሆን ለዚህም ቢሆን ምላሽ ተሰጥቶበታል፡፡ ክርክራቸውን በምሳሌ ሲያስረዱም ለደም ፈላጊዎች በነፃ የሚሰጠው ደም በገንዘብ የሚሸጥ ቢሆን ኖሮ የደም ለጋሾች ቁጥር የመመንመኑ ሁኔታ እውነትነት የለውም ይላሉ፡፡ ግን ልብ በሉ! ደም ሲለገስ በ48 ሰዓታት ውስጥ የሰውነታችን የደም መጠን ቀድሞ ወደነበረበት ሁኔታ ይመለሳል፡፡ ኩላሊት ግን አንድ ጊዜ ሄደ ማለት እስከ መጨረሻው ሄደ ማለት ነው፡፡ ከሚከፈለው መስዋእትነት አንፃር የኩላሊት ልገሳ አብዛኛውን ጊዜ የሚካሄደው በቂ ገንዘብ ኖሯቸው ለሰብዓዊ እርዳታ ብቻ ለመለገስ በሚወስኑ ግለሰቦች እንዲሁም በአንዳንድ ዘመዳሞችና ፍቅረኞች መካከል በመሆኑ እነዚህ ወገኖች ኩላሊት በገንዘብ የመሸጡ ነገር ሃሳባቸው ላያስቀይራቸው ይችላል፡፡ በተግባር እየታየ ካለው እውነታ አንፃር ሲታይ ይህ ምላሽ በፊት ለቀረበው ተቃውሞ በቂ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል፡፡
ይሁንና ክርክሩ መቋጫ አልተገኘለትም፡፡ ዋናውና መሰረታዊ ተደርጎ የተወሰደው የመከራከሪያ ነጥብ አስታራቂ ሃሳብ አልተገኘለትም፡፡ ጭብጡን በጥያቄ መልክ እንዲህ ላስቀምጠው ‹‹አንድ ሰው በራሱ ሰውነት ላይ ፍፁም ስልጣን አለው? ወይም ሊኖረው ይገባል?›› ለአንዳንዶች መልሱ በጣም ቀላል ነው፡፡ ‹አዎና!› ይላሉ ባለማመንታት ‹ከፈለግኩኝ እግሬን እቆርጠዋለሁ ቢያሻኝ አይኔን አውጥቼ እጥለዋለሁ፡፡ ማን ሊያገባው ይችላል?›
ሲያዩት ቀላል የሚመስለው ጥያቄ አከራካሪነቱ ገሃድ ወጥቶ የሚታየው ከፍትሐብሔር ህግጋት በተለይ ከውል ህግ መርሆዎች አንፃር ሲታይ ነው፡፡ የቅድሙ ጥያቄም መልኩን ቀይሮ ‹‹የተዋዋዩ ወገኖች ነፃት እስከ ምን ድረስ መሄድ አለበት? ወይም ኩላሊት ለመሸጥ የተደረገው ውል በፍርድ ቤት ተቀባይነት አግኝቶ መተግበር አለበት ወይ?›› የሚል አዲስ ገጽታ ያላብሳል፡፡ የተዋዋይ ወገኖች ነፃት ገደብ ምክንያቱ ግን ዞሮ ዞሮ አነስተኛ የመደራደር አቅም ያላቸውን ወገኖች ጥቅም ለማስጠበቅና ከለላ ለማድረግ እንዲሁም በዋነኛነት የህብረተሰቡን መልካም እሴትና ሥነ-ምግባ ሳይበረዝና ሳይበላሽ እንዲጠበቅ ሲባል ነው፡፡ ይህም ነጥብ በራሱ ወደ መጀመሪያ ላይ ወደ ነካካነውና ኩላሊትን መሸጥ ከሥነ-ምግባር አንጻር ተቀባይነት አለው ወይስ የለውም? ወደሚለው ሰፊ ክርክር መልሶ ይወስደናል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የንብረት ህግ ጽንሰ-ሓሳብ በራስ አካል ላይ ሰለሚኖር የባለቤትነት መብት (self-ownership) ላይ ተፈጻሚነት ይኖረዋልን? የሚል ጥያቄ እንድናነሳ ያስገድደናል፡፡ እኔም እስቲ እዚሁ ላይ ትቻችሁ ልሂድ፡፡ ለመሆኑ ኩላሊት ቢሸጥ አስነዋሪነቱ ምንድነው? የኩላሊት ሽያጭ በስፋት እየተከሰተ ያለው የሚበሉትና የሚጠጡት በሌላቸውና ድህነት የተስፋፋባቸው አካባቢዎች ከመሆኑ አንፃር ወደኛው ዘንድም የመምጣቱ አጋጣሚ ሰፊ ነውና ለጥያቄው ያላችሁን ወርውሩበት፡፡
የበላልበልሃን ብሎግ delete ማድረግ ተከትሎ በዛ ላይ ወጥተው የነበሩትን ጽሁፎች በዚህ ብሎግ ላይ በድጋሚ እንማወጣ ባስታወቁት መሰረት እነሆ አንድ የጠበቃ ቀልድ፡፡
አንድ ጠበቃዎችን በመኪና በመግጨት ራሱን የሚያዝናና የከባድ መኪና ሾፌር ነበር፡፡ ሁሌ በመንገድ ላይ ጠበቃ ሲያይ መኪናውን ያጠመዘዝና ያለርህራሄ ጠበቃውን ከገጨው በኋላ ‘ድው!’ የሚል የግጭት ድምጽ ሲሰማ አንጀቱ ይርሳል፡፡ አንድ ቀን መኪናውን እየነዳ ወደ ስራ ሲሄድ አንድ ቄስ መንገድ ዳር ቆመው ሲያይ ‘ዛሬ እንኳን ደግ ልስራ !’ ብሎ በማሰብ መኪናውን ያቆምላቸዋል፡፡
‹‹ወዴት ነው የሚሄዱት አባት?” ይጠይቃቸዋል፡፡
“ፊት ለፊት ወደአለችው ቤተክርስቲያን ነው ልጄ!” ቄሱ በትህትና መለሱለት፡፡
“ችግር የለም አባት ይግቡ እኔ እወስድዎታለሁ”
በሹፌሩ ደግነት የተደሰቱት ቄስ መኪና ውስጥ ገብተው ጉዞ ይጀምራሉ፡፡ በጉዞአቸው መሐል ሾፌሩ በመንገድ ዳር አንድ ጠበቃ ቦርሳውን ይዞ ሲሄድ ሲያይ ሳያውቀው በደመነፍስ መኪናውን በፍጥነት አዙሮ ወደ ጠበቃው መንዳት ይጀምራል፡፡ ሆኖም ከአጠገቡ የተቀመጡት ቄስ መሆናቸውን ሲያስብ የመኪናውን አቅጣጫ በማስቀየስ ጠበቃውን ለትንሽ ይስተዋል፡፡ ጠበቃው እንዳልተገጫ እርግጠኛ ቢሆንም “ድው!” የሚል ድምጽ ግን ሰምቷል፡፡ በፊት መስታወት ቢመለከትም የተገጨ ጠበቃ አልታየውም፡፡ በነገሩ ግራ የተጋባው ሾፌር “ይቅርታ ያድርጉልኝ አባቴ ያንን ጠበቃ እኮ ለትንሽ ገጭቼው ነበር!” ሲል ለቄሱ ይናዘዛል፡፡
ቄሱም በኩራት መንፈስ “ግድ የለህም ልጄ በበሩ አገጩን ብዬ ደፍቼዋለሁ!”
The Federal Supreme Court has released the table of contents of Cassation decisions volume 17.
Click the link below to download the file.
የጡረታ መውጫ እድሜ ላይ መድረስ ህጋዊ ውጤት
ሰራተኛው የጡረታ እድሜ ላይ ደረሶ ከተቀጣሪነት ወደ ተጧሪነት ሲሸጋገር የስራ ውሉም ያለ ተጨማሪ ቅድመ ሁኔታ ወዲያውኑ ያበቃለታል፡፡ ያ ማለት ግን ከጡረታ በኋላ እንደገና በአዲስ መልክ ተቀጣሪ ለመሆን አይችልም ማለት አይደለም፡፡ ጡረተኛው ካካበተው የረጅም ጊዜ የስራ ልምድ እና ተሞክሮ አንጻር በተለይ በአንዳንድ የስራ መስኮች ላይ ተፈላጊነቱ ይጨምራል፡፡ ሆኖም በቋሚነት (ላልተወሰነ) ጊዜ የመቀጠር እድል የለውም፡፡ በሰ/መ/ቁ 18832 (ቅጽ 6) እና 47469 (ቅጽ 9) በተሰጠ የህግ ትርጉም መሰረት ከጡረታ መውጣት በኋላ የሚደረግ የስራ ውል ለተወሰነ ጊዜ እንደተደረገ ይቆጠራል፡፡
ለመንግስትና ለግል ሰራተኞች በህግ የተቀመጠው የጡረታ እድሜ 60 ዓመት ሲሆን የሚሰላውም ሰራተኛው ለመጀመሪያ ጊዜ ሲቀጠር በቅድሚያ የመዘገበውን የልደት ዘመን መሠረት በማድረግ ነው፡፡
ሰራተኛው በህግ የተወሰነው የ60 ዓመት የጡረታ መውጫ እድሜ ላይ ሲደርስ የስራ ውሉን ያቋረጠው ህግ እንጂ አሰሪው ባለመሆኑ የስራ ውሌ ከህግ ውጪ ተቋርጧል በሚል የሚያነሳው ጥያቄ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ በአመልካች የኢትዮጵያ አገር አቋራጭ ከፍተኛ አውቶብስ የግል ባለንብረቶች ማህበር እና ተጠሪ አቶ አያሌው ይርጉ (ሰ/መ/ቁ 31402 ሚያዚያ 30 ቀን 2000 ዓ.ም ቅጽ 6) መካከል በሰበር በታየ ክርክር ተጠሪ የቀረብኝን እዳ ሳልከፍል በጡረታ ልገለል አይገባም በማለት በመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት እና በሰበር ችሎት ያቀረቡት ክርክር ተቀባይት ሳያገኝ ቀርቷል፡፡
በእርግጥ ሰራተኛው የጡረታ መውጫ እድሜ ላይ ከደረሰ በኋላ በጡረታ ሊገለል እንደማይገባ የሚያቀርበው ምክንያት የህግ ድጋፍ እንደሌለው አያከራክርም፡፡ በሰ/መ/ቁ 31402 በሰበር ችሎት በተሰጠው ውሳኔ ላይ ችሎቱ ለውሳኔው መሠረት ያደረገው ፍሬ ነገር ተጠሪ የጡረታ መውጫ እድሜያቸው ደርሶ በጡረታ ልገለል አይገባም በሚል ክስ እንዳቀረቡ ቢሆንም ለሰበር አቤቱታው መነሻ የሆነው የይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ውሳኔ ላይ የሰፈሩት ፍሬ ነገሮች ግን በዚህ መልኩ የተቃኙ አይደሉም፡፡ ስለሆነም ከግልጽነት አኳያ የጉዳዩን አመጣጥ በአጭሩ ማስቀመጥ ያስፈልጋል፡፡
ተጠሪ በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት ያቀረቡት ክስ በአመልካች መ/ቤት በገንዘብ ያዥነት ተቀጥሬ ስሰራ ገንዘብ በማጉደሌ መ/ቤቱ የስራ መደቤን ቀይሮ የቀረብኝን ብር 13,819.36 (አስራ ሶስት ሺ ስምንት መቶ አስራ ዘጠኝ ብር ከሰላሳ ስድስት ሳንቲም) እየሰራሁ ለመክፈል ተስማምቼ ሳለ ድርጅቱ እድሜዬ ከ60 ዓመት በላይ በመድረሱ ከስራ ተሰናብተሃል በማለት በስምምነታችን መሠረት እዳዬን ከፍዬ ሳልጨርስ ከስራዬ ያሰናበተኝ በመሆኑ ውዝፍ ደመወዝ ተከፍሎኝ ወደ ስራዬ እንድመለስ ይወሰንልኝ የሚል ነው፡፡
አመልካችም ለክሱ በሰጠው መልስ ተጠሪ በጡረታ ህጉ እና በድርጅቱ የአስተዳደር መመሪያ መሠረት በእድሜ ገደቡ ጡረታ ከወጡ በኋላ ወደ ስራዬ ልመለስ በማለት የሚጠይቁበት የህግ ስርዓት አለመኖሩን በመግለጽ የስራ ውሉ መቋረጥ በአግባቡ እንደሆነ ተከራክሯል፡፡ ፍ/ቤቱም ተጠሪ ከፍዬ ያልጨረስኩትን ገንዘብ ሳልከፍል መሰናበት የለብኝም በማለት ያቀረቡት መከራከሪያ በድርጅቱ ውስጥ ለመቆየት ዋስትና እንደማይሆን ገልጾ ክሱን ውድቅ አድርጎታል፡፡ በውሳኔው ቅር በመሰኘት ተጠሪ የይግባኝ አቤቱታ ለፌ/ከ/ፍ/ቤት ያቀረቡ ሲሆን ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን አከራክሮ የስር ፍ/ቤትን ውሳኔ በመሻር ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ ውሳኔው የሚከተለው ይዘት አለው፡፡
“ተጠሪው በድርጅቱ ሲቀጠሩ በጡረታ የተገለሉ መሆኑ ታውቆ ስራቸውን ጀምረው ሲሰሩ አንደገና 60 ዓመት የጡረታ እድሜ ስለደረሰ በማለት ለሁለተኛ ጊዜ በጡረታ ማሰናበቱ ከህጉ አግባብ ውጪ በመሆኑ ስንብቱ አላግባብ ነው፡፡”
የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ውሳኔ በሰበር ሲሻር ችሎቱ ለውሳኔው መሠረት ያደረገው ፍሬ ነገር በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት ከተገለጸው ጋር ተመሳሳይነት አለው፡፡ ሆኖም የይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ውሳኔ ይዘት ሲታይ ለውሳኔው መሠረት የተደረጉት ፍሬ ነገሮች ፈጽሞ የተለዩ ናቸው፡፡ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት እና የሰበር ችሎት ተጠሪ የጡረታ መውጫ 60 ዓመት ላይ ደርሰው በጡረታ ልገለል አይገባም በሚል ክስ እንዳቀረቡ ተደርጎ ውሳኔ የሰጡ ሲሆን በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ውሳኔ ላይ የተገለጸው ደግሞ ተጠሪ በጡረታ ከተገለሉ በኋላ በድጋሚ ተቀጥረው እንደገና በጡረታ ሊገለሉ እንደማይገባ ነው፡፡
የተጠሪ ጥያቄ እድሜዬ ለጡረታ የደረሰ ቢሆንም በጡረታ ልገለል አይገባም ከሆነ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት እና የሰበር ችሎት የሰጡት ውሳኔ የአዋጁን አንቀጽ 24(3) መሠረት ያደረገ በመሆኑ የሚነቀፍበት ምክንያት የለም፡፡ በተቃራኒው ጥያቄው የይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በቃኘው መልኩ ከጡረታ መገለል በኋላ የተፈጸመ የስራ ውል መቋረጥ ከሆነ አንቀጽ 24(3) ለጉዳዩ አግባብነት የለውም፡፡ በጡረታ የተገለለ ሰራተኛ ድጋሚ ሲቀጠር ለሁለተኛ ጊዜ በጡረታ የሚገለልበት ስርዓት ባለመኖሩም የይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ውሳኔ ሊነቀፍ አይገባውም፡፡ የሰበር ችሎቱ በፍሬ ነገር አገላለጽ ረገድ በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የተፈጸመ ስህተት ስለመኖሩ በውሳኔው ላይ አላመለከተም፡፡ ይህንን በግልጽ ባላመለከተበት ሁኔታ የሰጠው ውሳኔ የተሳሳተ ከመሆን አይድንም::
በጡረታ መገለል ሲባል ምን ማለት ነው?
“ሠራተኛው አግባብ ባለው ህግ መሠረት በጡረታ ሲገለል” የሥራ ውሉ በሕግ በተደነገገው መሰረት ይቋረጣል፡፡ ይህ የአንቀጽ 24(3) ድንጋጌ ግልጽነቱ ጎልቶ ይዘቱም ጠርቶ የሚታይ ይመስላል፡፡ ግልጽ ህግ አቃቂር ይወጣለት እንደሆን እንጂ ትርጉም አይሻም፡፡ ሆኖም ህግ የፈለገውን ያክል ግልጽነትን ተላብሶ መደንገጉ የአረዳድ ስህተት እንዳይፈጠር ዋስትና አይሰጥም፡፡ ምክንያቱም የችግሩ ምንጭ የአንባቢው እንጂ የተነባቢው አይደለምና፡፡ የአንቀጽ 24(3) ድንጋጌ በዚህ መነጽር ሲታይ እዚህ ደረጃ የሚደርስ ‘የተጋነነ’ ግልጽነት አለው ለማለት ባይቻልም ይዘቱ አከራካሪ የሚባሉ የአሰሪና ሰራተኛ ድንጋጌዎች ውስጥ የሚፈረጅ አይደለም፡፡
እንበልና የጡረታ እድሜ ላይ የደረሰ ሰራተኛ አሰሪው ስራ እንዲያቆም ሳይነግረው ስራ መስራቱን ቀጠለ፡፡ ሁለተኛው ወር ላይ አሰሪው በጡረታ ምክንያት ውሉ መቋረጡን አሳወቀው፡፡ በዚህን ጊዜ ውሉ የተቋረጠው መቼ ነው? የሚል ጥያቄ ይነሳል፡፡ ለጥያቄው በሁለት መልኩ ምላሽ ሊሰጥ ይችላል፡፡ በአንድ በኩል ጡረታ በህግ በተደነገገው መሰረት የስራ ውልን ስለሚያቋርጥ የስራ ውሉ ከሁለት ወራት በፊት በህግ ተቋርጧል፡፡ በሌላ በኩል ሰራተኛው ለጡረታ ዕድሜ ቢደርስም በአሰሪው አማካይነት ከስራ ካልተገለለ የመጀመሪያው ውል ቀጣይነት ስለሚኖረው ውሉ የተቋረጠበት ጊዜ ሁለተኛው ወር ላይ ነው ማለት ይቻላል፡፡
በጡረታ የመገለል ትርጉም በሰ/መ/ቁ 37551 (አመልካች አቶ ድካምየለህ ጥበቡ እና ተጠሪ አርሾ የሕክምና ላቦራቶሪ ኃላ/የተ/የግል ማህበር ታህሳስ 9 ቀን 2001 ዓ.ም. ቅጽ 8) አከራካሪ ጥያቄ ያስነሳ ቢሆንም የማያከራክር ምላሽ ግን አልተሰጠውም፡፡ በመዝገቡ ላይ ግራ ቀኙን ያከራከረው ጉዳይ መነሻው የስንብት ክፍያ ሲሆን የአመልካችን የስንብት ክፍያ መብት ለመወሰን የሥራ ውሉ የተቋረጠበት መንገድ ወሳኝ ጭብጥ ሆኖ በመውጣቱ በቅድሚያ እልባት ማግኘት ነበረበት፡፡ በተጠሪና የተጠሪ ሠራተኞች መካከል የተደረገው የህብረት ስምምነት ስራውን በገዛ ፈቃዱ ለለቀቀ ሠራተኛ የስንብት ክፍያ እንዲያገኝ ይፈቅዳል፡፡ አመልካች ከስር ፍርድ ቤት ጀምሮ የሚከራከሩት ስራቸውን በፈቃዳቸው የለቀቁ በመሆኑ በህብረት ስምምነቱ መሰረት የስንብት ክፍያ እንዲከፈላቸው ሲሆን ተጠሪ በበኩሉ የሥራ ውሉ የተቋረጠው አመልካች በጡረታ በመገለላቸው እንጂ ስራቸውን በመልቀቃቸው ባለመሆኑ ክፍያው እንደማይገባቸው በመግለጽ ክርክሩን አቅርቧል፡፡ ችሎቱ የግራ ቀኙን ክርክር አገናዝቦ ውሳኔ ለመስጠት እንዲረዳው መጀመሪያ በክርክሩ ሂደት የተረጋገጡ ያላቸውን ፍሬ ነገሮች ለይቶ አስቀምጧል፡፡
በዚሁ መሰረት አመልካች በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተቀጥረው ሲያገለግሉ ከቆዩ በኋላ እድሜያቸው 50 (ሃምሳ) ዓመት ሲሞላ በፈቃዳቸው ስራቸውን ለቀው ለዚህ አገልግሎታቸው የጡረታ መብት ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ ከዚህ መስሪያ ቤት ‘በጡረታ ከተገለሉ’ በኋላ በተጠሪ ድርጅት ከሐምሌ 19 ቀን 1989 ዓ.ም. ጀምሮ ተቀጥረው ለአስር ዓመታት ያህል አገልግለው እድሜ ለጡረታ ደርሷል በሚል ምክንያት ከነሐሴ 25 ቀን 1999 ዓ.ም. ጀምሮ ከሥራ መገለላቸው በችሎቱ እይታ የተረጋገጡ ጉዳዮች ናቸው፡፡
እዚህ ላይ ችሎቱ ፍሬ ነገሮቹን የገለጸበት መንገድ ትኩረትን የሚስብ ብቻ ሳይሆን ጥያቄም እንደሚያስነሳ ልብ ይሏል፡፡ “…ከዚህ መስሪያ ቤት በጡረታ ከተገለሉ በኋላ..” የሚለው አገላለጽ በክርክሩ ሂደት የተረጋገጠ ፍሬ ነገር አይደለም፡፡ ሊረጋገጥም አይችልም፡፡ ምክንያቱም በጡረታ መገለል በተያዘው ጉዳይ ላይ የህግ እንጂ የፍሬ ነገር ጉዳይ አይደለም፡፡ የክርክሩ ቁልፍ ጭብጥ የአመልካች የሥራ ውል የተቋረጠበት መንገድ ነው፡፡ አመልካች እንደሚሉት ሥራቸውን በገዛ ፈቃዳቸው ለቀው ከሆነ በህብረት ስምምነቱ መሰረት የስንብት ክፍያ ያገኛሉ፡፡ በተቃራኒው አግባብ ባለው ህግ በጡረታ የተገለሉ ከሆነ የፕሮፊደንት ፈንድ የተከፈላቸው በመሆኑ በድጋሚ የስንብት ክፍያ እንዳያገኙ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ (ማሻሻያ) አዋጅ ቁ. 494/1998 አንቀጽ 2(2) ሰ ይከለክላቸዋል፡፡ ከዚህ አንጻር የአመልካች በጡረታ መገለል ትርጉም የሚሻ የህግ ጥያቄ እንጂ በማስረጃ የሚረጋገጥ ፍሬ ነገር አይደለም፡፡
ችሎቱ ህግን ከፍሬ ነገር ቀላቅሎ ስህተት ከሰራ በኋላ በጉዳዩ ላይ የሚደርስበት ድምዳሜ ሆነ የሚሰጠው ውሳኔ የተሳሳተ እንደሚሆን መገመት አይከብድም፡፡ የአመልካች በጡረታ መገል አስቀድሞ ግምት የተወሰደበት በመሆኑ በተጠሪ የቀረበው ክርክር ተድበስብሶ ታልፏል፡፡ ይህንንም ከሚከተለው የችሎቱ ሐተታ ለመረዳት ይቻላል፡፡
“አመልካች ከተጠሪ ድርጅት የተሠናበቱት የጡረታ ዕድሜ ስለደረሰ ህጉም ስለሚያስገደዳቸው ጠይቀው ጡረታ ወጡ እንጂ ሥራ መልቀቅ ፈልገው አይደለም በማለት የተጠሪ ጠበቃ ያቀረቡት መከራከሪያ ሲታይ አመልካች ከጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በጡረታ የተገለሉ መሆኑ እየታወቀ በተጠሪ መስሪያ ቤት የተቀጠሩ መሆናቸው ጋር ተዳምሮ ሲታይ ተቀባይነት የሌለው ነው፡፡ በመሆኑም አመልካች በጡረታ ከተገለሉ በኋላ በተጠሪ መስሪያ ቤት ተቀጥረው ሲሠሩ ቆይተው ስራውን የለቀቁት በገዛ ፈቃዳቸው እንጂ የጡረታ ዕድሜ ደርሶ ሕጉ የሚያስገድዳቸው ሆኖ አይደለም፡፡ አመልካች ከተጠሪ መ/ቤት ስራቸውን የለቀቁት የጡረታ ዕድሜ ደርሶ ነው ቢባልም የጡረታ ዕድሜ የደረሰ ሠራተኛ የተጠሪን ድርጅት ለመልቀቅ ከፈለገ ሊከለከል የሚችልበት ምክንያት የለም፡፡”
ሐተታው እንደሚጠቁመን አመልካች ከጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በገዛ ፈቃዳቸው ስራቸውን ከለቀቁ በኋላ የጡረታ አበል ተጠቃሚ መሆናቸው በጡረታ ስለመገለላቸው ማረጋገጫ ሆኖ ተወስዷል፡፡ ይሁን እንጂ የጡረታ መውጫ ዕድሜ ከመድረሱ በፊት የጡረታ አበል ተጠቃሚ መሆን በአንቀጽ 24(3) አነጋገር ‘አግባብ ባለው ህግ መሰረት በጡረታ መገለል’ ማለት አይደለም፡፡ በመዝገቡ ላይ ውሳኔ የተሰጠው በ2001 ዓ.ም. ሲሆን በወቅቱ በመንግስት ሠራተኞች ላይ ተፈጻሚነት የነበረው የጡረታ ህግ የመንግስት ሰራተኞች የጡረታ አዋጅ ቁ 345/1995 ሲሆን ይኸው አዋጅ (ከነማሻሻያዎቹ) በአዋጅ ቁ 714/2003 እስከሚተካ ድረስ በአዋጅ ቁ 424/1997 እና በአዋጅ ቁ 633/2001 ተሻሽሏል፡፡
በአዋጅ ቁ 345/1995 አንቀጽ 12(1) ሐ የመንግስት ሰራተኞች የጡረታ መውጫ ዕድሜ (በእንግሊዝኛው ቅጂ ላይ retirement age) ስድሳ ዓመት እንዲሆን ተወስኗል፡፡ ጡረታ መውጣት ማለት ከስራ በጡረታ መገለል ማለት ነው፡፡ በዚህ አዋጅ ሆነ በአዲሱ አዋጅ ቁ. 714/2003 ብሎም በግል ድርጅት ሠራተኞች የጡረታ አዋጅ ቁ. 715/2003 አንድ ሠራተኛ የጡረታ መውጫ ዕድሜው ከመድረሱ በፊት ጡረታ የሚወጣበት ሆነ በጡረታ የሚገለልበት አግባብ የለም፡፡ ሆኖም ዕድሜው ለጡረታ ሳይደርስ የጡረታ አበል ባለመብትና ተጠቃሚ ሊሆን ይችላል፡፡ በአዋጅ ቁ 345/1995 አንቀጽ 12(2) እንደተደነገገው ቢያንስ ሃያ ዓመት ያገለገለ የመንግስት ሰራተኛ በራሱ ፈቃድ ወይም በአዋጁ ከተጠቀሱት ውጪ በሆነ ምክንያት አገልግሎት ካቋረጠ የጡረታ መውጫ ዕድሜው ሲደርስ የአገልግሎት ጡረታ አበል እስከ ዕድሜ ልኩ ይከፈለዋል፡፡ ድንጋጌው ሰራተኛውን የጡረታ አበል ተጠቃሚ ወይም ተከፋይ ሳይሆን የጡረታ ባለመብት ያደርገዋል፡፡ በዚህ መልኩ የሚገኝ የጡረታ ባለመብትነት በአዋጅ ቁ 714/2003 እና በአዋጅ 715/2003 ላይም በተመሳሳይ መልኩ ተደንግጓል፡፡ የሰራተኛው አገልግሎት ወይም የስራ ውሉ የተቋረጠው ሃያ አምስት ዓመት አገልግሎት ከሰጠ በኋላ ከሆነ የጡረታ መውጫ ዕድሜው ሊደርስ አምስት ዓመት ሲቀረው የጡረታ አበል ተጠቃሚነት ወይም ተከፋይነት መብት ይኖረዋል፡፡
የጡረታ መውጫ ዕድሜው ሊደርስ አምስት ዓመት ሲቀረው የጡረታ ክፍያ ማግኘት የጀመረ ሰራተኛ በድጋሚ ከተቀጠረ ውጤቱ ምን ይሆናል? ውጤቱ በድሮው አዋጅ ቁ 345/1995 መሰረት ሰራተኛው እንደገና በመንግስት መስሪያ ቤት ተቀጥሮ ደመወዝ ማግኘት ከጀመረ የጡረታ አበሉ ይቋረጣል፡፡ ሆኖም ዕድሜው ለጡረታ መውጫ እስኪደርስ ድረስ ያበረከተው አገልግሎት ከድሮው አገልግሎት ጋር ይደመርለታል፡፡ በድጋሚ የተቀጠረው በግል ድርጅት ከሆነ ግን የጡረታ አበል መቋረጥ ሆነ የአገልግሎት መደመር አይኖርም፡፡ አዋጁ የድጋሚ ቅጥር ውጤትን ለይቶ ያስቀመጠው ቅጥሩ በመንግስት መስሪያ ቤት ከተፈጸመ ብቻ ነው፡፡ በአዋጅ ቁ 714/2003 እና አዋጅ ቁ 715/2003 ደግሞ ድጋሚ ቅጥር ሲኖር እስከ ጡረታ መውጫ ዕድሜ ድረስ ያለው አገለግሎት ሰራተኛው በጡረታ አገልግሎት የሚታሰብለት ሲሆን ሲከፈለው የነበረው የጡረታ አበል ግን አይቋረጥም፡፡
በድሮው ሆነ በአሁኖቹ የጡረታ ህጎች ዳግም ቅጥር በጡረታ አገልግሎት ላይ ውጤት የሚኖረው ሰራተኛው ለጡረታ መውጫ ዕድሜ እስኪደርስ ድረስ ነው፡፡ ሰራተኛው ጡረታ የሚወጣበት ዕድሜ ላይ ከደረሰ በመንግስት መስሪያ ቤት ሆነ በግል ድርጅት ውስጥ የነበረው የስራ ውል ያለ ተጨማሪ ቅድመ ሁኔታ ይቋረጣል፡፡ የአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 24(3) ድንጋጌ ባይኖርም እንኳን ለጡረታ ዕድሜ ደርሶ ጡረታ መውጣት ማለት ስራ ማቆም፤ ከስራ ማረፍ፤ ስራ መተውና በህግ በተገኘ መብት መጦር ማለት በመሆኑ ስድሳ ዓመት መድረስ የሥራ ውልን እንደሚያቋርጥ የጡረታ ህጉን ብቻ መሰረት አደርጎ ድምዳሜ ላይ መድረስ ይቻላል፡፡ የጡረታ መውጫ ዕድሜ ስድሳ ዓመት ነው ከተባለ ሰራተኛው በጡረታ ከስራ የሚገለለው ወይም ጡረታ የሚወጣው ከስድሳ ዓመት በፊት ወይም ከስድሳ ዓመት በኋላ ሳይሆን ስድሳ ‘አናቷ’ ላይ ሲደርስ ብቻ ነው፡፡ መረሳት የሌለበት መሰረታዊ ነጥብ ግን የጡረታ ባለመብት ወይም ተጠቃሚ መሆን በጡረታ መገለል ማለት አለመሆኑ ነው፡፡
በሰ/መ/ቁ 37551 አመልካች በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ካገለገሉ በኋላ እድሜያቸው 50 (ሃምሳ) ዓመት ሲሞላ በፈቃዳቸው ስራቸውን ለቀዋል፡፡ በሆስፒታሉ ውስጥ ለሃያ አምስት ዓመታት ያህል አገልግለዋል ብለን ብንገምት እንኳን በወቅቱ በነበረው አዋጅ ቁ 345/1995 አንቀጽ 12(3) መሰረት የጡረታ አበል መቀበል የሚጀምሩት ሃምሳ አምስተኛው ዕድሜያቸው ላይ ነው፡፡ ስራቸውን የለቀቁት ሃያ ዓመታት አገልግለው ነው ቢባል ደግሞ በአዋጅ ቁ 345/1995 አንቀጽ 12(2) መሰረት የጡረታ አበል ሊከፈላቸው የሚችለው ድፍን ስድሳ ዓመት ሲሞሉ ነው፡፡ የጡረታ ባለመብት መሆን ብሎም የጡረታ አበል ማግኘት ማለት ጡረታ መውጣት ወይም በጡረታ መገለል ማለት አይደለም፡፡ ችሎቱ በጡረታ መገለልን ከጡረታ ባለመብትነትና ተጠቃሚነት ጋር ማደባለቁ ለስህተት ዳርጎታል፡፡
በ‘ህብረት ስምምነት’ በጡረታ መገለል
በህጉ የተቀመጠው የጡረታ መውጫ የዕድሜ ጣሪያ በስራ ውል ወይም በህብረት ስምምነት ዝቅ ወይም ከፍ ብሎ ሊወሰን አይችልም፡፡ የጡረታ ዕድሜን ለማሻሻል የሚደረግ ስምምነት በህግ ፊት ተቀባይነት እንደማይኖረው የሰበር ችሎት በሰ/መ/ቁ. 80079 (አመልካች አቶ ጥላሁን ታችበሌ እና ተጠሪ ግሎባል ሆቴል ኃ/የተ/የግ/ማህበር ህዳር 19 ቀን 2005 ዓ.ም. ቅጽ 14) የህግ ትርጉም ሰጥቶበታል፡፡
የክርክሩ መነሻ አመልካች ከህግ ውጭ መሰናበታቸውን በመግለጽ ተገቢ ክፍያዎች እንዲከፈላቸው በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ያቀረቡት ክስ ሲሆን ተጠሪም በተከሳሽነት ቀርቦ በድርጅቱ የህብረት ስምምነት አንቀጽ 32.5 መሰረት የተጠሪን ጡረታ የመውጫ ዕድሜ የመወሰን ስልጣን የተሰጠው በመሆኑና አመልካችም ዕድሜያቸው 55 ዓመት የሞላቸው በመሆኑ ስንብቱ በህብረት ስምምነቱ መሰረት በአግባቡ ነው የሚል መከራከሪያ አቅርቧል፡፡ ፍርድ ቤቱም ስንብቱ በህብረት ስምምነቱ መሰረት የተፈጸመ ህጋዊ ነው በማለት ውሳኔ የሰጠ ሲሆን ይግባኝ የቀረበለት ከፍተኛ ፍርድ ቤትም የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ አጽንቶታል፡፡
አመልካችም የጡረታ ዕድሜ በህግ እንጂ በህብረት ስምምነት ሊወሰን እንደማይገባ በመግለጽ የሰበር አቤቱታ አቅርበዋል፡፡ አቤቱታውን የመረመረው የሰበር ችሎት ውሳኔ ሲሰጥ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 24(3) ሰራተኛው አግባብ ባለው ህግ በጡረታ ሲገለል የስራ ውሉ እንደሚቋረጥና በሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞች አዋጅ ሆነ በግል ሰራተኞች የጡረታ አዋጅ ቁጥር 715/2003 አንቀጽ 17(1) የጡረታ መውጫ ዕድሜ 60 ዓመት መሆኑን ካተተ በኋላ የተጠቀሰው የህብረት ስምምነት ከአዋጁ የበለጠ መብት የማይሰጥ በመሆኑ አዋጁ ተፈጻሚነት ሊሰጠው እንደሚገባ አቋም ይዟል፡፡ የስራ ውሉ መቋረጥም ከህግ ውጭ ነው በማለት የስር ፍርድ ቤቶችን ውሳኔ ሽሯል፡፡
በ‘መንግስት ውሳኔ’ በጡረታ መገለል
በሰ/መ/ቁ 42906 እና በሰ/መ/ቁ 98099 (አመልካቾች እነ ወ/ሮ ድንቄ ኦዳ (29 ሰዎች) እና ተጠሪ የኢትዮጵያ ፐልፕና ወረቀት አክስዮን ማህበር ሰኔ 19 ቀን 2006 ዓ.ም. ቅጽ 16) መደበኛው የጡረታ ዕድሜ ላይ ያልደረሰ ሠራተኛ በመንግስት ማለትም በሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ በጡረታ የሚገለልበት ስርዓት እንዳለ ግምት ተወስዶ በሰበር ችሎት ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡ ለመሆኑ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ይህን መሰሉ ስልጣን የሚሰጥ አግባብነት ያለው ህግ አለ? የድሮው ሆነ የአሁኑ የጡረታ ህግ አንድ የመንግስት ሆነ የግል ድርጅት ሰራተኛ የጡረታ ዕድሜ ላይ ሳይደርስ የጡረታ ባለመብት ወይም የጡረታ ተጠቃሚ የሚሆንበትን ሁኔታ እንጂ ዕድሜው ሳይደርስ ጡረታ የሚወጣበትን ወይም በጡረታ የሚገለልበትን ልዩ ሁኔታ አላስቀመጠም፡፡
በሰ/መ/ቁ 98099 ቁጥራቸው 29 የሚሆኑ ሠራተኞች በአዋጅ ቁ 714/2003 አንቀጽ 17 የሚኒስትሮች ምክር ቤት የጡረታ መብት እንዲጠበቅላቸው ወስኗል በማለት የጡረታ መውጫ ዕድሜያቸው ሳይደርስ የስራ ውላቸውን ከህግ ውጭ እንዳቋረጠው በመግለጽ የተለያዩ ክፍያዎች እንዲከፈላቸው የጠየቁ ሲሆን ተጠሪ በበኩሉ ለክሱ በሰጠው መልስ አመልካቾች በጠቀሱት የአዋጁ ድንጋጌ መሰረት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ የጡረታ መብት ተጠብቆላቸው የተሰናበቱ ስለሆነና በዚህ መልኩ ለተሰናበተ ሠራተኛ የስንብት ክፍያ ሆነ ካሳ የሚከፈልበት የሕግ አግባብ የሌለ መሆኑን ዘርዝሮ ክሱ ውድቅ ሊደረግ እንደሚገባ ተከራክሯል፡፡
ክሱ የቀረበለት ፍርድ ቤት አመልካቾች በአዋጅ ቁ 714/2003 ስለሚተዳደሩ ጉዳዩን ለማየት የዳኝነት ስልጣን እንዳልተሰጠው በመግለጽ ክሱን በብይን ውድቅ ያደረገው ሲሆን ይግባኝ የቀረበለት ፍርድ ቤትም ይግባኙን ሰርዞታል፡፡ በአመልካቾች የሰበር አቤቱታ የቀረበለት የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ደግሞ አመልካቾች ያቀረቡተ ክስ በፍርድ ሊታይ የሚችል አይደለም በማለት የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ ምክንያቱን ቀይሮ ውጤቱን አጽድቆታል፡፡
ጉዳዩ ወደ ፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ሲደርስ ጉዳዩ በፍርድ ቤት ሊታይ የሚችልና በመደበኛው ፍርድ ቤት የዳኝነት ስልጣን ስር እንደሚወድቅ ችሎቱ ከስር ፍርድ ቤቶች የተለየ አቋም በመያዝ ብይኑን ውድቅ አድርጎታል፡፡ ሆኖም የብይኑ ውድቅ መደረግ የብይኑን መሻር አላስከተለም፡፡ በዋናው ጉዳይ ላይ በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠ ውሳኔ ሳይኖር ችሎቱ በፍሬ ነገሩ ላይ ውሳኔ በመስጠቱ ብይኑ በውጤት ደረጃም ቢሆን ተቀባይነት አግኝቷል፡፡ የሰበር ችሎት በስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ባላረፈበት ጉዳይ ላይ ውሳኔ እንዳይሰጥ በአዋጅ ቁ 25/88 እና በህገ መንግስቱ ስልጣኑ ተገድቧል፡፡ አንድ ጉዳይ በሰበር ሊታይ የሚችለው በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠ የመጨረሻ ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት እንደተፈጸመበትና እንዳልተፈጸመበት አጣርቶ ተገቢውን የህግ ትርጉም በመስጠት ለማረም ነው፡፡ የህግ ትርጉም ለመስጠት መጀመሪያውኑ በስር ፍርድ ቤት የተሰጠ ውሳኔ መኖር አለበት፡፡ በስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ባላረፈበት ጉዳይ በሰበር ችሎት የሚሰጥ የህግ ትርጉም ሆነ ውሳኔ በይዘቱ ትክክል ቢሆንም ባይሆንም መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሞበታል፡፡ ስልጣን በሌለበት ትክክለኛነት የለምና፡፡
ችሎቱ በዋናው ጉዳይ ላይ ውሳኔ መስጠቱ ስህተት መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ የውሳኔም ይዘትም እንዲሁ ከስህተት የጸዳ አይደለም፡፡ ውሳኔውን ለመተቸት በመጀመሪያ ደረጃ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የተጠሪዎችን የሥራ ውል አቋርጧል ወይስ አላቋረጠም? የሚለው መሰረታዊ ጥያቄ የማያሻማ መልስ ማግኘት ይኖርበታል፡፡ ተጠሪ በአዋጅ ቁ 714/2003 አንቀጽ 17(9) ድንጋጌ አግባብ አመልካቾች በጡረታ እንዲገለሉ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ማስወሰኑ እንዳልተካደና አመልካቾችም ጉዳዩ በሚኒስትሮች ምክር ቤት መወሰኑን አምነው እንደሚከራከሩ በሐተታው ላይ ተገልጿል፡፡ በውሳኔው መግቢያ ላይ በአጭሩ ተቀንጭቦ የቀረበው የአመልካቾች ጥያቄና የተጠሪ ምላሽ ግን በሐተታው የተገለጸውን አያንጸባርቅም፡፡ በውሳኔው መግቢያ ላይ የሰፈረውና ለክርክሩ መነሻ የሆነው የአመልካቾች ክስ በአዋጅ ቁ 714/2003 አንቀጽ 17 የሚኒስትሮች ምክር ቤት የጡረታ መብት እንዲጠብቅላቸው ወስኗል በማለት የጡረታ መውጫ ዕድሜያቸው ሳይደርስ የስራ ውላቸውን ከህግ ውጭ እንዳቋረጠው በመግለጽ የተለያዩ ክፍያዎች እንዲከፈላቸው ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ ተጠሪም አመልካቾች በሚኒስትሮች ምክር ቤት በተወሰነው መሰረት የጡረታ መብት ተጠብቆላቸው የተሰናበቱ ስለሆነ ጥያቄያቸው ተቀባይነት እንደሌለው በመግለጽ ምላሽ መስጠቱ ተመልክቷል፡፡ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የተወሰነው አመልካቾች የጡረታ መብት እንዲጠበቅላቸው ነው ወይስ የጡረታ መብት ተጠብቆላቸው እንዲሰናበቱ? ለዚህ ጥያቄ ሁለቱንም አማራጭ መልሶች በመያዝ የሥራ ውሉን መቋረጥ ከአሠሪና ሠራተኛ አዋጁ ድንጋዎች አንጻር እንደሚከተለው እንፈትሻለን፡፡
ከዚያ በፊት ግን በአዋጅ ቁ 714/2003 አንቀጽ 19(7) የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስልጣንና ሚና ምን እንደሆነ እናያለን፡፡ የአዋጅ ቁ 714/2003 አንቀጽ 19(7) ድንጋጌ እንደሚከተለው ይነበባል፡፡
“…የመንግስት መስሪያ ቤቱ ህልውና በማክተሙ፤ የሰው ኃይል ብዛቱ ከሚፈልገው በላይ በመሆኑ ወይም ከፕራይቬታይዜሽን ጋር በተያያዘ ከስራ እንዲሰናበተ ከተደረገና አገልግሎቱ ከ25 ዓመት ያላነሰና ዕድሜው ከ50 ዓመት ያላነሰ ከሆነ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ሲወሰን የአገልግሎት የጡረታ አበል እስከ ዕድሜ ልክ ይከፈለዋል፡፡” (ስርዝ የተጨመረ)
በድንጋጌው ላይ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስልጣንና የህጉ ዓላማ ብሎም በምክር ቤቱ የሚወሰነው ጉዳይ ምን እንደሆነ ግልጽ ብሎ ይታያል፡፡ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ የሚሰጠው በደንጋጌው በተጠቀሱት ምክንያቶች የተሰናበተ ሰራተኛ አገልግሎቱ ከ25 ዓመት ያላነሰና ዕድሜው ከ50 ዓመት ያላነሰ ከሆነ የአገልግሎት የጡረታ አበል እንዲከፈለው ብቻ ነው፡፡ ስለሆነም የስንብቱ መኖር ከምክር ቤቱ ውሳኔ ይቀድማል፡፡ ምክር ቤቱ በድንጋጌው መሰረት የተሰናበተን ሰራተኛ የጡረታ መብት እንዲያስጠብቅ እንጂ ስራ ላይ ያለን ሰራተኛ እንዲያሰናብት አልተፈቀደለትም፡፡ ስልጣንም አልተሰጠውም፡፡
በአዋጅ ቁ 714/2003 አንቀጽ 19(7) ሰራተኛው የሚሰናበትባቸው ምክንያቶች በግልጽ ተቀምጠዋል፡፡ ከአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁ 377/96 አንጻር ካየናቸው የመንግስት መስሪያ ቤቱ ህልውና ማክተም በአንቀጽ 24(4) በህግ በተደነገገው መሰረት የስራ ውልን የሚያቋርጥ በቂ ምክንያት ሲሆን የሰው ኃይል ብዛቱ መስሪያ ቤቱ ከሚፈልገው በላይ መሆኑ ደግሞ በአንቀጽ 28 ወይም እንደሚሰናበተው ሰራተኛ ቁጥር በአንቀጽ 28 እና 29 የስራ ውልን በማስጠንቀቂያ ብሎም ተጨማሪ የሆነው የአንቀጽ 29 ስርዓት ሲሟላ የሥራ ውል ይቋረጣል፡፡ ፕራይቬታይዜሽን በራሱ የስራ ውል ማቋረጫ ምክንያት አይደለም፡፡
የአዋጁ አንቀጽ 23(2) በባለቤትነት መተላለፍ ሰበብ የስራ ውል ማቋረጥን በግልጽ ይከለክላል፡፡ ሆኖም አንድ የመንግስት የልማት ድርጅት ወደ ግል ከመዛወሩ በፊት ወይም በኋላ የሰራተኖች ቅነሳ ሊደረግ ይችላል፡፡ ከፕራይቬታይዜሽን ጋር በተያያዘ የሚኒስትሮቸ ምክር ቤት ሚና የሚመጣው በአሠሪና ሠራተኛ አዋጁ በአንዱ ወይም በሌላኛው ምክንያት የስራ ውል ከተቋረጠ በኋላ ነው፡፡ ስለሆነም ‘በሚኒስትሮች ምክር ቤት በጡረታ መገለል’ የሚለው አገላለጽ ፈሩን የሳተና ከህጉም አንጻር ተጨባጭነት የሌለው ነገር ነው፡፡
በሰ/መ/ቁ 98099 የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ የአመልካቾችን የጡረታ አበል ተጠቃሚነት ብቻ በማረጋገጥ የተሰጠ ውሳኔ ከሆነ ተጠሪ ይህንን ውሳኔ መሰረት በማድረግ ብቻ የአመልካቾችን የስራ ውል ሊያቋጥ አይችልም፡፡ የምክር ቤቱ ውሳኔ ተጠሪ ሠራተኞችን ካሰናበተ በኋላ የሚመጣ እንጂ በራሱ የስንብቱ በቂ ምክንያት አይደለም፡፡ ስለዚህ አመልካቾች በህጉ አግባብ የሚቀነሱ ከሆነ ተጠሪ በህጉ በተዘረጋው የቅነሳ ስርዓት ቅነሳ አድርጎ ማስጠንቀቂያ ወይም የማስጠንቂያ ጊዜ ክፍያ ከፍሎ እንዲሁም በቅነሳ ምክንያት የሚከፈለውን ካሳ እና የስንብት ክፍያ ለሰራተኞቹ ከፍሎ በአጠቃላይ በአሠሪና ሠራተኛ ህጉ መሰረት ሙሉ መብታቸውንና ጥቅማቸውን ጠብቆ የስራ ውላቸውን በህጋዊ መንገድ ማቋረጥ አለበት፡፡ ይህ በሌለበት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔን ለስራ ውሉ መቋረጥ እንደ ምክንያት መጥቀስ አይችልም፡፡
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ካለ ስልጣኑ የአመልካቾች የሥራ ውል እንዲቋረጥ ትዕዛዝ ሰጥቶ ከሆነ የአመልካቾች የሥራ ውል ከህግ ውጭ መቋረጡ ብዙም አከራካሪ አይሆንም፡፡ አመልካቾች የሥራ ውል የመሰረቱት ከተጠሪ ጋር እንጂ ከሚኒስትሮች ምክር ቤት ጋር አይደለም፡፡ ስለሆነም የምክር ቤቱ ውሳኔ እንደ ምክንያት ለመቅረብ እንኳን ብቁ አይደለም፡፡ በተጨማሪም ምክር ቤቱ በአዋጅ ቁ 714/2003 አንቀጽ 19(7) የተሰጠው ስልጣን ሰራተኛን እንዲያሰናብት ሳይሆን የተሰናበተን ሠራተኛ የጡረታ አበል ተጠቃሚነት እንዲያረጋግጥ ብቻ ነው፡፡
ሕጉ የሚለው ይህ ከሆነ ቀጥለን የሰበር ችሎት የሚለው ምን እንደሆነ እንመልከት፡፡ በውሳኔው ላይ የአመልካቾች የሥራ ውል መቋረጥ ህጋዊ ነው የተባለበት የሐተታ ክፍል እንደሚከተለው ይነበባል፡፡
“አመልካቾች በአዋጅ ቁ 714/2003 አንቀጽ 19(7) መሰናበታቸው ከተረጋገጠ ይኼው ውሳኔ በሕጉ በተዘረጋው ስርዓት መሰረት እስካልተለወጠ ድረስ በአዋጅ ቁ 377/96 መሰረት ስንብቱ ህገ ወጥ ነው በማለት የሚከራከሩበት አግባብ የለም፡፡”
አሁንም ለመድገም ያክል ችሎቱ በጠቀሰው አዋጅ ቁ 714/2003 አንቀጽ 19(7) መሰረት የሚኒስትሮች ምክር ቤት የሚሰጠው ውሳኔ ሠራተኛው በድንጋጌው ላይ ተለይተው በተቀመጡት ምክንያቶች በአሠሪና ሠራተኛ ህጉ (ሠራተኛው በመንግስት ሰራተኞች ህግ ቁ 515/1999 የሚገዛ ከሆነ ደግሞ በዚሁ ህግ) መሰረት የሥራ ውሉ ሲቋረጥ የጡረታ አበል ተጠቃሚ እንዲሆን እንጂ የሥራ ውሉን በቀጥታ በማቋረጥ የጡረታ አበል ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረግ አይደለም፡፡ ግልጽ መሆን ያለበት ነገር አዋጅ ቁ 714/2003 አንቀጽ 19(7) ለሠራተኛው ተጨማሪ ከለላና ጥበቃ የሚያደርግ ድንጋጌ እንጂ አሠሪው በአሠሪና ሠራተኛ አዋጁ የተዘረጋውን የሥራ ውል ማቋረጥ ስርዓት በአቋራጭ ‘ሸውዶ እንዲያልፍ’ የሚያመቻች ድንጋጌ አይደለም፡፡
Statutory Definitions | Ethiopian Legal Brief.
Click on the alphabets to browse.
A B C D E F G H I J K L M N O P Q R S T U V W X Y Z
Statutory Definitions, is a new page added to the blog. It is placed next to the About page on the Home menu. It contains alphabetical list of some statutory definitions.
The statutory definitions are taken from a compilation titled “Dictionary of judicial and Statutory Definitions of Legal Terms” (Unpublished, 300 Pages). The compilation comprises of all words and phrases defined by the House of People’s Representatives and the Council of Ministers. It also includes judicial definitions by the Cassation Bench of the Federal Supreme Court and definitions found in the CODEs.
Brief note on how to use:
1. Abbreviations
P=Proclamation
R=Regulation
Hence:
(P331/03) is to mean Proclamation Number 331/2003 and (R17/97) stands for Regulation Number 17/1997. A Table of Legislation is provided in the compilation to identify the full title of proclamations and regulations.
2. Terms having similar definitions are separated by a comma. For instance, the statutory definition for academic staff is provided in the following way:
Academic Staff
(R60/99, R61/99, R62/99, R63/99, and R68/01) means any employee engaged in teaching or research activities
This indicates that academic staff is defined similarly in regulations number 60, 61, 62, 63 and 68.
3. When one word is defined differently, the definitions are listed in their order of publication on the relevant statutes.
For instance, here is how the definitions of ‘beneficiary’ are listed.
Beneficiary
(R91/2003, R154/2008) means a student at a public higher education institution pursuing higher education or training and who has entered into an obligation with the concerned institution for the future payment of the cost of his/her education or training and other services
(P653/09) means a Head of State or Government, Senior Government Official, Member of Parliament or Judge who is enjoying or entitled to the rights and benefits under this Proclamation
(P690/10) means a person entitled to receive the benefit packages under the social health insurance scheme
(P714/2011) means a public servant or his survivor who receives benefits or fulfils the conditions for receiving benefits in accordance with this Proclamation
(P715/2011) means an employee of private organization or his survivor who receives benefits or fulfils the conditions for receiving benefits
(P780/2013) means a person who receives benefits or profits, or is designated as the recipient of funds or other property
This shows that similar definitions are provided for beneficiary in regulations number 91 and 154. However, the term is defined differently in proclamations number 653, 690, 714, 715 and 780.
For instance let’s have a look at the statutory definition of Rights to Lien:
Rights to Lien (P372/03) it is a preferential rights of the warehouse man over the goods stored in a warehouse or over the pledgee [pleadgee] of warehouse receipts [recipts] or over the bailer or his transferee on the proceeds earned from sale of the goods, in relation to the cost incurred pursuant [persuant] to the provision of this proclamation to store, deposit prepare pack, transport, insure and for Labour and professional work and incurred to properly [preperly] handled the goods and sale including [includily] the unpaid and remaining warehouse cost
The words pleadgee, recipts, persuant, preperly, includily all appear on the legislative text (i.e. proclamation number 372/03).
ማውጫ
ከአምስት ያላነሱ ዳኞች
ምንም ምክንያት የሌለው ውሳኔ
በቅጽ ውስጥ ያልተካተቱ (ያልታተሙ) ውሳኔዎች
ወደኋላ ተመልሶ ስለመስራት (retro-activity)
የህግ ትርጉም መለወጥ
ሰበር ውሳኔ የሰጠበት ህግ ‘ሲሻር’ የውሳኔው የአስገዳጅነት ውጤት
የሰበር ውሳኔ አስገዳጅነት ፡የሰበር ውሳኔዎች ዳሰሳ
ከአምስት ያላነሱ ዳኞች
የሰበር ችሎት የህግ ትርጉም በስር ፍርድ ቤቶች አስገዳጅነት የሚኖረው ከአምስት ያላነሱ ዳኞች በተሰየሙበት የተሰጠ እንደሆነ ነው፡፡ [አዋጅ ቁ 454/1997 የፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅን እንደገና ለማሻሻል የወጣ አዋጅ አንቀጽ 2(1) ] ለሰበር የሚቀርብ አቤቱታ በዋናው ችሎት ከመታየቱ በፊት ሶስት ዳኞች በተሰየሙበት አጣሪ ችሎት ያስቀርባል ተብሎ ትዕዛዝ መሰጠት አለበት፡፡ [አዋጅ ቁ 25/88 አንቀጽ 22(1)] አቤቱታው አያስቀርብም ከተባለ ውድቅ ተደርጎ መዝገቡ ይዘጋል፡፡ አያስቀርብም የሚል ትዕዛዝ የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ለሰበር የሚያበቃ መሰረታዊ ስህተት እንደሌለበት ከሚያመለክት በስተቀር እንደ ህግ ትርጉም አይቆጠርም፡፡ ይህም የአጣሪ ዳኞች ቁጥር ከአምስት ማነሱ ጋር ተዳምሮ ሲታይ ያስቀርባል/አያስቀርብም የሚል ትዕዛዝ በስር ፍርድ ቤቶች አስገዳጅነት እንደለሌለው ይጠቁመናል፡፡
በአመልካች የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረቶች ጽ/ቤት እና ተጠሪ አቶ ጥበበ አየለ (ግንቦት 13 ቀን 2003 ዓ.ም. ሰ/መ/ቁ 59025 ቅጽ 12) መካከል በነበረው ክርክር በተመሳሳይ ጉዳይ ላይ አመልካች ያቀረበው የሰበር ቅሬታ ለሰበር ችሎቱ አያስቀርብም ተብሎ በመዘጋቱ የተያዘውም ጉዳይ በተመሳሳይ መንገድ መስተናገድ እንደሚገባው በተጠሪ በኩል ክርክር ቀርቧል፡፡ ችሎቱም በሶስት ዳኞች በአጣሪ ችሎት የሚሰጠው ትዕዛዝ አስገዳጅነት እንደሌለው በመጠቆም የተጠሪን ክርክር ውድቅ አድርጎታል፡፡
የሰበር አቤቱታ ያስቀርባል ከተባለ በኋላ ከሞላ ጎደል በሁሉም ጉዳዮች ክርክር የሚታየው በአምስት ዳኞች ነው፡፡ ሆኖም አንዳንድ ጊዜ በጣም መሰረታዊ የሆነ የህግ ትርጉም የሚያስነሳ ጉዳይ ሲኖር እንዲሁም ችሎቱ በፊት የነበረውን አቋም በግልጽ ሲቀይር ጉዳዩ የሚታየው በሰባት ዳኖች ነው፡፡ ሰባት ዳኞች በተሰየሙበት በሰበር ችሎት ከተሰጡ ውሳኔዎች መካከል ሰ/መ/ቁ 29181 [አመልካች የኢትዮጵ ንግድ ባንክ እና ተጠሪ እነ አቶ ልየው ቸኮል (2 ሰዎች) ታህሳስ 20 ቀን 2002 ዓ.ም. ቅጽ 10] 34329 [አመልካች የኢትዮጵ ንግድ ባንክ እና ተጠሪ እነ አቶ ፈቃደ ደምስስ (2 ሰዎች) ታህሳስ 20 ቀን 2002 ዓ.ም. ያልታተመ] 39362 [አመልካች እነ አቶ ንጉሴ ታምራት (6 ሰዎች) እና ተጠሪ በከልቻ ትራንስፖርት አክስዮን ማህበር ታህሳስ 12 ቀን 2002 ዓ.ም. ያልታተመ] እንዲሁም 42239 [አመልካች ብሔራዊ ማዕድን ኮርፖሬሽን ኃላ.የተ.የግል ኩባንያ እና ተጠሪ ዳኒ ድሪሊንግ ኃላ.የተ.የግል ኩባንያ ጥቅምት 29 ቀን 2003 ዓ.ም. ቅጽ 10] ይገኙበታል፡
ምንም ምክንያት የሌለው ውሳኔ
የሰበር ችሎት የሚሰጠው የህግ ትርጉም አስገዳጅነት በህግ የተወሰነ እንደመሆኑ የስር ፍርድ ቤቶች ቢያምኑበትም ባያምኑበትም መቀበልና ተፈጻሚ የማድረግ ግዴታ አለባቸው፡፡ ሆኖም በህግ መደንገጉ ብቻውን የሰበር ችሎት ውሳኔ በስር ፍርድ ቤቶች ሙሉ ተቀባይነትና ተፈጻሚነት ኖሮት ወጥነትና ተገማችነትን ለማስፈን ዋስትና አይሆንም፡፡ ስለሆነም የአስገዳጅነት ኃይል በህግ ብቻ ሳይሆን በአሳማኝነት ኃይል መታገዝ ይኖርበታል፡፡ ምክንያት የሌለው ብሎም ምክንያታዊ ያልሆነ ውሳኔ የአሳማኝነት ኃይል አይኖረውም፡፡ ይህ ደግሞ የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔውን እንዳላዩ በማለፍ ተቃራኒ ውሳኔ እንዲሰጡና ተመሳሳይ ጉዳዮች የችሎቱን በር እንዲያጣብቡ በር ይከፍታል፡
በፍርድ ቤት በሚሰጥ ውሳኔ ላይ በዋነኛነት የተያዘውን ጭብጥ፤ ጭብጡ እንዴት እንደተወሰነና የተወሰነበትን ምክንያት መግለጽ አለበት፡፡ [የፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 182(1)] ምክንያት የሌለው ውሳኔ መሰረታዊ ጉድለት አለበት፡፡ በተለይ በሰበር ችሎት የሚሰጥ ውሳኔ ሁልጊዜም ቢሆን ምክንያት ሊኖረው ይገባል፡፡ ችሎቱ ምክንያት መስጠት ያለበት የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ ሲሽር ብቻ አይደለም፡፡ ውሳኔውን ለማጽናትም ምክንያት ያስፈልጋል፡፡
ይህንን የውሳኔ አጻጻፍ መርህና ስርዓት በሚጣረስ መልኩ የሰበር ችሎት በሰ/መ/ቁ 27162 (አመልካች ወ/ሮ እሸት መሐመድ እና ተጠሪ ዘይነባ አህመድ ጥቅምት 25 ቀን 2001 ዓ.ም. ያልታተመ) የሰጠው ውሳኔ እንደሚከተለው ይነበባል፡፡
“ለዚህ ችሎት ጥቅምት 23 ቀን 1999 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ የቀረበው የሰበር አቤቱታ ለተጠሪ ደርሶ ሐምሌ 2ዐ ቀን 1999 ዓ.ም. የተፃፈ የመልስ ማመልከቻ አቅርቧል፡፡
የግራ ቀኙን ክርክር አቤቱታው ከቀረበበት ውሣኔ መደምደሚያና ለዚህም መሠረት ከሆነው የሕግ ትንታኔ አንፃር ተመርምሮ ውሣኔው ጉድለት የሌለበት ሆኖ ስለተገኘ በከፍተኛ ፍ/ቤት በመዝገብ ቁጥር 41534 በሐምሌ 17 ቀን 1998 ዓ.ም የተሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ 348/1/ መሠረት ፀንቷል፡፡ ይፃፍ ግራ ቀኙ ኪሣራቸውን ለየራሣቸው ይቻሉ፡፡ መዝገቡ ተዘግቷል፡፡ ይመለስ፡፡”
ከዚህ ውሳኔ ጋር ተመሳሳይነት ባለው መልኩ በሰ/መ/ቁ 39403 [አመልካች እነ ወ/ሮ ሄርሜላ ውድነህ እና ተጠሪ መሠረት ሀብታሙ ሐምሌ 3 ቀን 2003 ዓ.ም. ያልታተመ] ፤ 24515 [አመልካች እነ አቶ ሐብቴ ዙርጋ እና ተጠሪ እነ አቶ ሙሉሸዋ ተፈራ ጥቅምት 20 ቀን 2001 ዓ.ም. ያልታተመ] ፤ 16239 [አመልካች እነ አቶ ኃይሉ ቶላ እና ተጠሪ አቶ ግርማ ሁሪሣ ታህሳስ 26 ቀን 1999 ዓ.ም. ያልታተመ] ፤ 16614 [አመልካች ኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ ኃ/የተ/የግ/ማ/ እና ተጠሪ እነ አቶ ተዘራ ዘለቀ ኃዳር 28 ቀን 1999 ዓ.ም. ያልታተመ] ፤ እና 16842 [አመልካች አቶ ተሰማ ዘረፋ እና ተጠሪ አቶ አብሴ ዓለሙ ወራሾች ታህሳስ 19 ቀን 1999 ዓ.ም. ያልታተመ] ፤ አንዳችም ምክንያት ሳይቀርብ ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡
በጣም የሚገርመው የውሳኔዎቹ ምክንያት አልባነት ብቻ ሳይሆን ከግማሽ ገጽ የምታንስ ውሳኔ ለመጻፍ ከአንድ ዓመት እስከ ሶስት ዓመት መፍጀቱ ነው፡፡ በውሳኔዎቹ ላይ አቤቱታ የቀረበበትና ውሳኔ የተሰጠበት ቀን ያለው ልዩነት ትንሹ አንድ አመት ሲሆን ትልቁ ደግሞ ሶስት ዓመት ነው፡፡ ሌላው አስገራሚው ነገር ደግሞ የሰ/መ/ቁ 24515 ሶስት ለሁለት በሆነ አብላጭ ድምጽ የተሰጠ ሲሆን ጥልቅ በሆነ የህግ ትንተና ተደግፎ አስር ገጽ የልዩነት ሓሳብ በውሳኔው ላይ ሰፍሯል፡፡ የዚህ ልዩነት ተገላቢጦሹ ደግሞ በሰ/መ/ቁ 3915 [አመልካች የኢትዮ/አየር መንገድ እና ተጠሪ አቶ እንደርታ መስፍን ሚያዝያ 22 ቀን 2002 ዓ.ም. ያልታተመ] ታይቷል፡፡ በዚህ መዝገብ የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ አራት ለአንድ በሆነ አብላጨ ድምጽ የተሻረ ሲሆን አነስተኛው ድምጽ ለመለየት የሰጠው ምክንያት “የስር ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ባለመሆኑ…” የሚል ነው፡፡ በእርግጥ ይህ ምክንያት አይደለም፡፡ የምክንያት አለመኖር እንጂ፡
በቅጽ ውስጥ ያልተካተቱ (ያልታተሙ) ውሳኔዎች
የሰበር ችሎት ውሳኔ ቀላልና አመቺ በሆነ መንገድ ለስር ፍርድ ቤቶች እንዲደርስ ካልተደረገ በተመሳሳይ ጉዳዮች ላይ ጥራትና ወጥነት ያለው ፍርድ አይኖርም፡፡ የፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅን እንደገና ለማሻሻል የወጣው አዋጅ ቁ 454/1997 አንቀጽ 2(1) የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስገዳጅ የህግ ትርጉም የተሰጠባቸውን ውሳኔዎች በየደረጃው ላሉ ፍርድ ቤቶችና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት አሳትሞ እንደሚያሰራጭ ይደነግጋል፡፡ ይህ በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ላይ የተጣለው ግዴታ ከሰበር ውሳኔ አስገዳጅነት ጋር በተያያዘ አከራካሪ ጥያቄ ያስነሳል፡፡ እስከአሁን ድረስ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት አስገዳጅ የህግ ትርጉም የተሰጠባቸውን ውሳኔዎች በአስራ ስድስት ቅጾች አሳትሞ አሰራጭቷል፡፡ ሆኖም ቅጾቹ ሁሉንም የሰበር ውሳኔዎች ያካተቱ አይደለም፡፡ ይህ ደግሞ በቅጽ ውስጥ ያልተካተቱ (ያልታተሙ) ውሳኔዎች በአዋጁ መሰረት አስገዳጅ ናቸው? የሚል ጥያቄ ያስነሳል፡፡
እስካሁን ድረስ ጥያቄው በሰበር ችሎት የህግ ትርጉም አልተሰጠውም፡፡ ሆኖም ችሎቱ ራሱ ያልታተሙ ውሳኔዎችን ሲጠቅስ ይስተዋላል፡፡ የሰ/መ/ቁ 44218 [አመልካች የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን እና ተጠሪ እነ አቶ ታጁ አባጋሮ (21 ሰዎች) ግንቦት 13 ቀን 2003 ዓ.ም. ቅጽ 9] ችሎቱ በሰ/መ/ቁ 43197 የሰጠውን አስገዳጅ የህግ ትርጉም ይጠቅሳል፡፡ ሆኖም 43197 በቅጽ ውስጥ የለም፡፡ በሰ/መ/ቁ. 39580 [አመልካች አልታቤ ኮሌጅ እና ተጠሪ ሠይድ መሐመድ ግንቦት 18 ቀን 2001 ዓ.ም ያልታተመ] እንዲሁ ችሎቱ የሰ/መ/ቁ 39579ን በመጥቀስ ውሳኔ የሰጠ ቢሆንም የሰ/መ/ቁ 39579 በቅጾቹ ውስጥ አልተካተተም፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ችሎቱ በሰ/መ/ቁ 42901 (ቅጽ 8) ላይ በሰ/መ/ቁ 40055 የሰጠውን ተመሳሳይ የሕግ ትርጉ የሚጠቅስ ቢሆንም ይህ የተጠቀሰው የሰበር ውሳኔ በቅጾቹ ውስጥ አልተካተም፡፡ የችሎቱ አካሄድ በቅጽ ያልተካተተ ውሳኔ የአስገዳጅነት ኃይል እንዳለው የተቀበለው ይመስላል፡፡
ወደኋላ ተመልሶ ስለመስራት (retro-activity)
የሰበር ውሳኔ አስገዳጅ መሆን የሚጀምረው ከመቼ ጀምሮ ነው? የሰበር ውሳኔ በትርጉም የሚፈጠር ራሱን የቻለ ህግ ነው፡፡ በተወካዮች ምክር ቤት የሚወጣ አዋጅና በሚኒስትሮች ምክር ቤት የሚወጣ ደንብ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተፈጻሚነት ያገኛል፡፡ በመርህ ደረጃ ህግ ወደ ኋላ ተመልሶ አይሰራም፡፡ በተለይ በወንጀል ህግ ይህ መርህ ህገ መንግስታዊ መሰረት ያለው ነው፡፡ በፍትሐ ብሔር ጉዳይም ቢሆን ቀድመው የተከናወኑ ህጋዊ ተግባራት ውጤትና አፈጻጸም ብዙውን ገዚ በ’መሸጋገሪያ ድንጋጌዎች’ በግልጽ ተለይቶ ይወሰናል፡፡
የሰበር ውሳኔ እንደ ማናቸውም የፍርድ ቤት ውሳኔ ሁሉ ተጽፎና በአስቻሉት ዳኞች ተፈርሞ ለተከራካሪ ወገኖች በይፋ ከተነበበት ቀን ጀምሮ የጸና (ውጤት ያለው) ይሆናል፡፡ [ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 181(1)] ሆኖም የሰበር ውሳኔ በተከራካሪ ወገኖች ላይ ከሚኖረው ውጤት በተጨማሪ በስር ፍርድ ቤቶችም ላይ የአስገዳጅነት ውጤት አለው፡፡ በስር ፍርድ ቤቶች ላይ አስገዳጅነቱ መቼ እንደሚጀምር ራሱን የቻለ የህግ ትርጉም የሚፈልግ ጥያቄ ነው፡፡ ጥያቄው በዋነኛነት በውሳኔው መታተምና አለመታተም ላይ ያጠነጥናል፡፡ በዚህ ነጥብ ላይ በሰበር ችሎት የተሰጠ የህግ ትርጉም ባይኖርም ከላይ በቅጽ ውስጥ ያልተካተቱ ውሳኔዎች አስመልክቶ እንዳየነው ያልታተመ ውሳኔ በችሎቱ ሳይቀር መጠቀሱ ህትመት ቅድመ ሁኔታ ስላለመሆኑ ተቀባይነት አግኝቷል ለማለት እንችላለን፡፡ ስለሆነም የሰበር ችሎት ውሳኔ በይፋ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ አስገዳጅነት ይኖረዋል ብሎ መደምደም የሚያስኬድ ነው፡፡
የሰበር ውሳኔ አስገዳጅነት ወሰኑ በስር ፍርድ ቤቶች ላይ የተገደበ ነው፡፡ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ እንደሚወጣ ህግ በማናቸውም የፌደራል ወይም የክልል ህግ አውጪና አስፈጻሚ እንዲሁም ማንኛውም የተፈጥሮ ሰውና በህግ የሰውነት መብት በተሰጠው አካል [የፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁ 3/1987 አንቀጽ 2(3)] ላይ አስገዳጅነት የለውም፡፡ አስገዳጅነቱ በስር ፍርድ ቤቶች ላይ ብቻ መሆኑ ወደ ኋላ ተመልሶ ከመስራት ጋር በተያያዘ ሁለት መሰረታዊ ቁምነገሮች ያስጨብጠናል፡፡
ይኸውም፤
“…ውሳኔ የሚያሻቸው ጉዳዮች ዓይነት ከዚህ በፊት በፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችሎት ቀርበው ትርጉም ተሰጥቶባቸው ከሆነ በሀገሪቱ ወጥ የሆነ የሕግ አተረጓጎምና አፈጻጸም ማስፈን እንዲቻል በተመሣሣይ ታይተው እንዲወሰኑ ለማድረግ እንዲቻል እንጂ ሥርዓቱን አሟጦ በውሳኔ የተቋጨን ጉዳይ ሁሉ እንደገና እየቀሰቀሱ የተረጋጋውን ሁኔታ ለማናጋት ወይም ተከራካሪ ወገኖችን ተገማች ላልሆነ የዳኝነት ስርዓት ለመጋበዝ ተፈልጎ አይለም፡፡”
(አመልካች አቶ ጌታቸው ደያስ (ሁለት ሰዎች) እና ተጠሪ ወ/ሮ ሩቅያ ከድር መጋቢት 12 ቀን 2004 ዓ.ም. ሰ/መ/ቁ 68573 ቅጽ 13)
የህግ ትርጉም መለወጥ
የሰበር ውሳኔ አስገዳጅነቱ ለስር ፍርድ ቤቶች እንጂ ለራሱ ለችሎቱ አይደለም፡፡ ችሎቱ በሌላ ጊዜ በተመሳሳይ ጭብጥ የተለየ ትርጉም ሊሰጥ ይችላል፡፡ ምንም እንኳን የሰበር ችሎቱ በሌላ ጊዜ በተመሳሳይ ጭብጥ የተለየ ትርጉም መስጠት ቢችልም በጠባቡ ካልተተገበረ የሰበር ውሳኔ በስር ፍርድ ቤቶች ሊኖረው የሚገባውን የተሰሚነትና የተቀባይነት ደረጃ በእጅጉ ዝቅ ያደርገዋል፡፡ መረሳት የሌለበት ነገር ወጥነት ለስር ፍርድ ቤቶች ብቻ ሳይሆን ለራሱ ለችሎቱም በእጅጉ ያስፈልገዋል፡፡ በአንድ ጭብጥ ላይ በየጊዜው የሚቀያየር የሰበር ውሳኔ በስር ፍርድ ቤቶች ዘንድ ተፈጻሚነቱ አጠያያቂ ነው፡፡ ስለሆነም በአንድ ጭብጥ ላይ ወዲያው ወዲያው በሰበር ችሎት የአቋም ለውጥ በሚኖር ጊዜ የስር ፍርድ ቤቶችን ከማደናገሩም በላይ የውሳኔውን የተሰሚነት ደረጃ ዝቅተኛ ያደርገዋል፡፡ በተመሳሳይ ጭብጥ የተለየ ትርጉም መስጠት እጅግ አስፈላጊ የሚያደርጉ ሁኔታዎች ወይም ምክንያቶች መኖራቸው እስካልተረጋገጠ ድረስ አንድ ጊዜ የተሰጠ ውሳኔ ፀንቶ ሊቆይ ይገባል፡፡ የተለየ ትርጉም ሲያስፈልግ ለውጥ ማድረግ የተፈለገበትን ምክንያት በአዲሱ ውሳኔ ላይ በግልጽ ማመልከትና የበፊቱን ውሳኔ በማያሻማ መልኩ በግልጽ መሻር ያስፈልጋል፡፡
በግልጽ የሚደረግ የትርጉም ለውጥ ያልተገባ ውዥንብርን ያስወግዳል፡፡ በአነስተኛ ወጪ ፍትሕ በቀላሉ እንዲሰፍንም ያደርጋል፡፡ የቀድሞ የህግ ትርጉም በግልጽ ቀሪ ተደርጎ አዲስ አቋም ከተያዘባቸው መዝገቦች መካከል ሰ/መ/ቁ 42239 [አመልካች ብሔራዊ ማዕድን ኮርፖሬሽን ኃላ.የተ.የግል ኩባንያ እና ተጠሪ ዳኒ ድሪሊንግ ኃላ.የተ.የግል ኩባንያ ጥቅምት 29 ቀን 2003 ዓ.ም. ቅጽ 10] ፤ 43821 [አመልካች ወ/ሮ ትርሐስ ፍስሐዬ እና ተጠሪ ወ/ሮ ዘነበች በሪሁን ጥር 5 ቀን 2002 ዓ.ም. ቅጽ 9 ] እና 36730 [አመልካች የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን እና ተጠሪ አቶ አማረ ገላው ሐምሌ 30 ቀን 2002 ዓ.ም. ቅጽ 9] ተጠቃሽ ናቸው፡፡ በሰ/መ/ቁ 36730 የግልግል ዳኝነት ጉባኤ የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ እንደሆነ ስምምነት ከተደረገ በሰበር ችሎት ሊታይ አይችልም በማለት በሰ/መ/ቁ 21849 ተሰጥቶ የነበረው የህግ ትርጉም ተሸሮ ችሎቱ የጉባኤውን ውሳኔ ለማየት ስልጣን እንዳለው ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡ በሰ/መ/ቁ 43281 ዳኝነት እንደገና እንዲታይ ጥያቄው መቅረብ ያለበት ይግባኝ ከመቅረቡ በፊት እንደሆነ በሰ/መ/ቁ 16624 ተሰጥቶ የነበረው የህግ ትርጉም ተለውጦ ከይግባኝ በኋላም ሊቀርብ እንደሚችል አቋም ተይዞበታል፡፡ የሰመ/ቁ 36730 የይርጋ ማቋረጫ ምክንያትን የሚመለከት ሲሆን ከዚህ ቀደም በሰ/መ/ቁ 16648 ስልጣን ለሌለው የዳኝነት አካል ክስ ማቅረብ የይርጋ ጊዜን እንደማያቋርጥ ተደርጎ ህጉ መተርጎሙ አግባብነት እንደሌለው ታምኖበት ይርጋን እንደሚያቋርጥ የህግ ትርጉም ተሰጥቶበታል፡፡
የትርጉም ለውጥ በተደረገባቸው ሶስቱም መዝገቦች ውሳኔ የተሰጠው ሰባት ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት ነው፡፡ ይህም የትርጉም ለውጥ ከሚደረግበት ስርዓት ጋር በተያያዘ ጥያቄ እንድናነሳ ያስገድደናል፡፡ ሰባት ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት የተሰጠ የህግ ትርጉም ከሰባት ያነሱ ለምሳሌ አምስት ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት ሊለወጥ ይችላል? የዳኞች ቁጥር እንደተጠበቀ ሆኖ በሙሉ ድምጽ የተሰጠ ውሳኔ በአብላጭ ድምጽ ሊለወጥ የመቻሉ ጉዳይም ሌላው በጥያቄነት መነሳት ያለበት ነው፡፡
ሰበር ውሳኔ የሰጠበት ህግ ‘ሲሻር’ የውሳኔው የአስገዳጅነት ውጤት
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችሎት ውሳኔ በስር ፍርድ ቤቶች ላይ የአስገዳጅነት ውጤት እንዲኖረው በህግ የተደነገገው በ1997 ዓ.ም. ሲሆን የሰበር ችሎት የዚህን አዋጅ መውጣት ተከትሎ በሰበር ስልጣኑ የሚሰጣቸው ውሳኔዎች በፌደራልና በክልል የስር ፍርድ ቤቶች ላይ የአስገዳጅነት ውጤት አግኝተዋል፡፡ ሆኖም በአዋጅ ቁ 454/1997 ላይ የድንጋጌ ለውጥ ሳይኖር የአንድ አዋጅን መሻር ተከትሎ በሰበር ትርጉም የተሰጠበት ውሳኔ የሚኖረው ህጋዊ ውጤት በህጉ አፈፃፀም ላይ በተግባር የሚያጋጥም ችግር ሆኗል፡፡
በእርግጥ ሰበር ትርጉም የሰጠበት ህግ ተሸሮ ትርጉም የተሰጠበት ድንጋጌም ቀሪ ወይም ውጤት የሌለው በሚሆንበት ጊዜ ውሳኔውም ያለ አንዳች ቅድመ-ሁኔታ ለቀጣይ ተመሳሳይ ጉዳዮች የአስገዳጅነት ውጤት ሊኖረው እንደማይችል ግልጽ ነው፡፡ ለምሳሌ አዋጅ ቁጥር 639/2001 ለባንክ ወይም ለአነስተኛ የፋይናንስ ተቋም ብድር መያዣነት የተሰጠ የማይንቀሳቀስ ንብረትን የሚመለከት ውል በፍርድ ቤት መዝገብ ወይም ስልጣን በተሰጠው አዋዋይ ፊት መፈረም እንደማያስፈልገው በመደንገግ በፍትሐ ብሔር ህግ ቁጥር 1723 ስር የተመለከተውን ቅድመ-ሁኔታ በከፊል ቀሪ አድርጎታል፡፡ ስለሆነም የሰበር ችሎት ከዚህ አዋጅ መውጣት በፊት የፍትሐ ብሔር ህግ ቁጥር 1723ን መሰረት በማድረግ ለባንክ ወይም ለአነስተኛ የፋይናንስ ተቋም ብድር መያዣነት የተሰጠ የማይንቀሳቀስ ንብረትን የሚመለከት ውልን በመተርጎም የሰጣቸው ውሳኔዎች በስር ፍርድ ቤቶች የአስገዳጅነት ውጤት አይኖራቸውም ማለት ነው፡፡
ይሁን እንጂ አንዳንድ ጊዜ አንድ አዋጅ ሙሉ በሙሉ ተሽሮ በአዲስ አዋጅ ሲተካ በተሻረው አዋጅና በአዲሱ አዋጅ የሚገኙ የተወሰኑ ድንጋጌዎች ምንም ዓይነት የይዘት ለውጥ አይደረግባቸውም፡፡ ለዚህ ጥሩ አብነት የሚሆነን የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 42/85 በ377/96 መተካት ነው፡፡ ምንም እንኳን አዋጅ ቁጥር 42/85 በ377/96 የተሻረ ቢሆንም በቀድሞው አዋጅ ላይ የነበሩ ብዙ ድንጋጌዎች ምንም ዓይነት የይዘት ለውጥ አልተደረገባቸውም፡፡ ለምሳሌ የአዋጁን የተፈጻሚነት ወሰን የሚመለቱ ድንጋጌዎች፤ የስራ ውል አመሰራረትን የሚመለከቱ ድንጋጌዎች፤ የስራ ውል የሚቆይበትን ጊዜ አስመልክቶ የተቀመጡ ድንጋጌዎች (አዲስ ንዑስ አንቀጾች ከመጨመራቸው ውጪ የቀድሞ ድንጋጌዎች አልተቀየሩም) እንዲሁም ሌሎች ብዙ ድንጋጌዎች ይዘታቸው አልተቀየረም፡፡
እዚህ ላይ ጥያቄ ይነሳል፡፡ የይዘት ለውጥ ባልተደረገበት አንቀጽ ላይ አዋጅ ቁጥር 42/85ን መሰረት በማድረግ በሰበር የተሰጠ ውሳኔ አዋጁ በ377/96 ከተሻረ በኋላም የአስገዳጅነት ውጤት አለው? በዚህ ነጥብ ላይ የሰበር ችሎት በሁሉም ዓይነት የስራ ክርክር፤ የፍትሐብሔር፤ የወንጀልና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ወጥ በሆነ መልኩ ተፈፃሚነት ያለው ውሳኔ ያልሰጠ ቢሆንም የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይን በተመለከተ ግን በከፊልም ቢሆን ምላሽ ሰጥቶበታል፡፡ ስለሆነም በአዋጅ ቁጥር 42/85 መሰረት የተሰጠ የሰበር ውሳኔ አዋጅ ቁጥር 377/96 ከወጣ በኃላ በአዲሱ አዋጅ መሰረት የሚነሱ የስራ ክርክሮች ላይ የሚኖረውን ህጋዊ ውጤት በከፊልም ቢሆን ምላሽ ያገኘ ይመስላል፡፡
በአመልካች ሐመረ ወርቅ ቅ/ማሪያም ቤተክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት እና መልስ ሰጭዎች እነ ዲያቆን ምህረተ ብርሐን (6 ሰዎች) (ግንቦት 4 ቀን 1998 ዓ.ም ሰ/መ/ቁ 18419 ቅጽ 8) በነበረው የአሰሪና ሰራተኛ ክርክር ሰበር ችሎቱ የተያዘውን ጉዳይ ብቻ አስመልክቶ እንዳለው አዋጅ ቁጥር 42/85 በአዋጅ ቁጥር 377/96 የተሻረ ቢሆንም ነጥቡን በሚመለከት ሁለቱ አዋጆች አንድ አይነት ድንጋጌዎችን የያዙ በመሆኑ ችሎቱ የአዋጅ ቁጥር 42/85 ድንጋጌዎችን መሰረት አድርጎ በተጠቀሰው ነጥብ ላይ የሰጠው የህግ ትርጉም ለአዋጅ ቁጥር 377/96 ድንጋጌዎችም አግባብነት ያለው ነው፡፡
የመጨረሻ ውሳኔ፡ የሰበር ችሎት ውሳኔዎች ዳሰሳ
በአዋጅ ቁ. 25/88 አንቀጽ 10 በሰበር ችሎት ስልጣን ስር የሚወድቁ ጉዳዮች በስር ፍርድ ቤት በይግባኝ ወይም በመደበኛ ስልጣን የመጨረሻ ውሳኔ የተሰጠባቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ የመጨረሻ ውሳኔ ሲባል ምን ማለት እንደሆነ በአዋጁ ትርጓሜ አልተሰጠውም፡፡ በአንቀጽ 10(2) የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት መደበኛ ችሎት ግራ ቀኙን አከራክሮ ውሳኔ ሲሰጥ ውሳኔ መሰጠቱ በራሱ የመጨረሻ የሚያደርገው በመሆኑ የመጨረሻ ፍርድ ትርጉም ከዚህኛው ድንጋጌ አንጻር አደናጋሪ አይሆንም፡፡ የይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ውሳኔም የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ ሙሉ በሙሉ በመሻር ወይም በማጽናት ከተሰጠ የይግባኝ አቅራቢውን ተከራካሪ ወገን ማንነት መሰረት በማድረግ ውሳኔው የመጨረሻ ስለመሆኑ መለየት አይከብድም፡፡ መሰረታዊው ቁምነገር አንድ ተከራካሪ ወገን ከአንድ ጊዜ በላይ ይግባኝ የማቅረብ መብት የሌለው መሆኑ ነው፡
ይሁን እንጂ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ በከፊል በማሻሻል ውሳኔ ሲሰጥ ውሳኔው በከፊል የመጨረሻ ፍርድ ያገኘ፤ በከፊል ደግሞ ያላገኘ ስለሚሆን በአንቀጽ 10(1) እና (2) መሰረት የሰበር ችሎቱን ስልጣን ለመወሰን አስቸጋሪ ያደርገዋል፡፡ ይኼው ነጥብ በሰ/መ/ቁ 61480 (አመልካች ገ/እግዚአብሔር ከበደው እና ተጠሪ ወ/ት ሠላማዊት ወ/ገብርዔል ጥቅምት 22 ቀን 2004 ዓ.ም. ቅጽ 13) የተነሳ ሲሆን የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ተሻሽሎ በከፊል መለወጡ የመጨረሻ እንደሚያደርገው የህግ ትርጉም ተሰጥቶበታል፡፡ ሆኖም በዚህ መልኩ የህግ ትርጉም መስጠት ሊያስከትል የሚችለው የጎንዮሽ ችግር እንዴት እንደሚፈታ ችሎቱ በመፍትሔነት ያሰቀመጠው ነገር የለም፡
በመዝገቡ ላይ አመልካች በትግራይ ክልል የወረዳ ፍ/ቤት ተከሳሽ የነበሩ ሲሆን ተጠሪ ደግሞ ከሳሽ ናቸው፡፡ የወረዳው ፍርድ ቤት ተጠሪ (የስር ከሳሽ) የጠየቁትን ዳኝነት በሙሉ በመቀበል ብር 213450 (ሁለት መቶ አስራ ሶስት ሺ አራት መቶ ሃምሳ ብር) እንዲከፈላቸው ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ አመልካች (የስር ተከሳሽ) በውሳኔው ቅር በመሰኘት ለመቐሌ ዞን ከፍተኛው ፍርድ ቤት የይግባኝ አቤቱታ አቅርበው ፍርድ ቤቱም አመልካች ለክሱ ኃላፊ ናቸው የተባለበትን የስር ፍርድ ቤት የውሳኔ ክፍል ሳይቀይር ለተጠሪ እንዲከፈል የተባለውን የገንዘብ መጠን ግን በግማሽ ቀንሶ 123450 ብር (አንድ መቶ ሃያ ሶስት ሺ አራት መቶ ሃምሳ ብር) አመልካች እንዲከፍሉ ውሳኔ ሰጥቷል፡
አመልካች በዚህኛውም ውሳኔ ባለመስማማት የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔዎች መሰረታዊ የህግ ስህተት እንደተፈጸመባቸው በመግለጽ የሰበር አቤቱታ ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አቅርበዋል፡፡ የክልሉ ሰበር ችሎት የስር ፍርድ ቤቶች በጉዳዩ ላይ የተለያየ ውሳኔ እንደሰጡ በመጠቆም የመጨረሻ ውሳኔ ሳይኖር አመልካች የሰበር አቤቱታ ሊያቀርቡ አይችሉም በማለት አቤቱታውን ባለመቀበል መዝገቡን ዘግቶታል፡ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የመጨረሻ የሚባል ፍርድ ስለመኖሩ ጉዳዩን ከክልሉ ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ አንጻር የፈተሸው ሲሆን የወረዳውና ከፍተኛው ፍርድ ቤት የአመልካችን ኃላፊነት አስመልክቶ ተመሳሳይ ውሳኔ የሰጡ በመሆኑ ጉዳዩ የመጨረሻ ውሳኔ የተሰጠው ነው ሊባል እንደሚገባ ድምዳሜ ላይ ደርሷል፡፡ ምንም እንኳን መዝገቡ የታየው ከክልሉ ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ አንጻር ቢሆንም አዋጁ ከአዋጅ ቁ. 25/88 አንቀጽ 10 ጋር ተመሳሳይነት ባለው መልኩ የክልሉን ሰበር ሰሚ ችሎት የሰበር ስልጣን የሚወስን በመሆኑ በችሎቱ የተሰጠው የህግ ትርጉም ለችሎቱ ለራሱ ሳይቀር ፋይዳ አለው፡
ከላይ ለመግለጽ እንደተሞከረው በችሎቱ የተሰጠው የህግ ትርጉም የጎንዮሽ ችግሮችን ለመፍታት አያስችልም፡፡ የከፍተኛው ፍርድ ቤት በማሻሻል የሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ የሚሆነው ለአመልካች እንጂ ለተጠሪ አይደለም፡፡ ውሳኔው ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት የተወሰነላቸውን የገንዘብ መጠን በግማሽ ቀንሶታል፡፡ ተጠሪ በውሳኔው ቅር ተሰኝተው ይግባኝ ሊያቀርቡ የሚችሉት ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እንጂ ለሰበር ችሎቱ አይደለም፡፡ ይህ መሆኑ ደግሞ አንድና ተመሳሳይ ጉዳይ በአንድ ጊዜ በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤትና በክልሉ ሰበር ችሎት እንዲታይ ያደርገዋል፡፡ በዚህን ጊዜ የሰበር ችሎቱ መዝገቦቹን ማጣመር አለበት? ወይስ ተጠሪ ማቅረብ የሚችሉት መስቀለኛ የሰበር አቤቱታ ነው? በዚህ መልኩ አቤቱታ ማቅረብ መቻላቸው በራሱ የህግ ምላሽ የሚፈልግ ጥያቄ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ተጠሪ የይግባኝ አቤቱታ እንጂ መስቀለኛ የሰበር አቤቱታ ማቅረብ ፍላጎቱ ከሌላቸውስ? የተጠሪ የይግባኝ መብት የሚፈጸመው እንዴት ነው? በሰ/መ/ቁ 61480 እነዚህና መሰል ጥያቄዎች በጥልቀት ተመርምረው እልባት አላገኙም፡፡ ከዚህ አንጻር የችሎቱ ውሳኔ ራሱ የመጨረሻ ፍርድን አስመልከቶ የመጨረሻ እልባት የሰጠ ውሳኔ ነው ለማለት አይቻልም፡
ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ ሙሉ በሙሉ በማጽናት ወይም በመሻር ውሳኔ ቢሰጥም ይግባኝ አቅራቢውን ተከራካሪ ወገን በተመለከተ የመጨረሻ ፍርድ የማይሆንባቸው አጋጣሚዎች ይኖራሉ፡፡ ይህም የሚሆነው የይግባኝ አቤቱታው ከመነሻው ይግባኝ የማይባልበት ጉዳይ ከሆነ ነው፡፡ ለምሳሌ በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ 184 የትዕዛዝ ይግባኝ ስላለመኖሩ ተደንግጓል፡፡ በድንጋጌው ስር በተዘረዘሩት ጉዳዮች ላይ የይግባኝ አቤቱታ ቀርቦ አቤቱታው ቢሰረዝ ወይም ቢጸና የይግባኝ ሰሚውን ውሳኔ እንደ መጨረሻ ፍርድ በመቁጠር የሰበር አቤቱታ ሊቀርብ አይችልም፡፡
በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ 184 ከተካተቱት ውስጥ ተከሳሽ በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ 141(1) መሰረት እንዲከላከል የሚሰጥ ትዕዛዝ የማይገኝ ሲሆን በሌሎች ድንጋጌዎች ላይም በትዕዛዙ ላይ ይግባኝ ማቅረብ ስለመቻሉ/ስላለመቻሉ በግልጽ የተቀመጠ ነገር የለም፡፡ ሆኖም የሰበር ችሎት ከወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ 184 እና 185 ጣምራ ንባብ በመነሳት ተከሳሽ እንዲከላከል በተሰጠው ትዕዛዝ ላይ ይግባኝ ማቅረብ እንደማይችል መጀመሪያውኑ ይግባኝ ማቅረብ በማይችልበት ጉዳይ ይግባኝ አቅርቦ ይግባኙ ቢሰረዝ የይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ትዕዛዝ/ውሳኔ የመጨረሻ ፍርድ ሊባል እንደማይገባ በሰ/መ/ቁ 74041 (አመልካች እነ አንተነህ መኮንን እና ተጠሪ የፌደራል ስነ-ነግባርና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን ዓቃቤ ህግ ሰኔ 4 ቀን 2004 ዓ.ም. ቅጽ 13) የህግ ትርጉም ሰጥቷል፡፡
በተመሳሳይ መልኩ በወንጀል ጉዳይ ተከሳሽ በሌለበት ፍርድ ሲሰጥ ክርክሩ እርሱ ባለበት እንዲታይ አቤቱታ አቅርቦ ውድቅ ካላስደረገውና አቤቱታው ተቀባይነት ካጣ በሌለበት ታይቶ የተሰጠው ፍርድ እንደመጨረሻ ፍርድ ተቆጥሮ በሰበር ሊታረም አይችልም፡፡ (አመልካች ሰማኸኝ በለው እና ተጠሪ የፌደራል ዐቃቤ ህግ ታህሳስ 25 ቀን 2003 ዓ.ም. ሰ/መ/ቁ 57632 ቅጽ 12 በተጨማሪም ሰ/መ/ቁ 59537 ቅጽ 12 እና 74041 ቅጽ 13 ይመለከቷል፡፡)
ከክልል የሚነሱ ጉዳዮች በሰበር ሊታዩ የሚችሉት የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመደበኛ ችሎት ወይም በይግባኝ አይቶ የመጨረሻ ውሳኔ የሰጠባቸው ጉዳዮች ሲሆኑ ነው፡፡ (አዋጅ ቁ 25/88 አንቀጽ 10(3) የጉዳዩ ዓይነት የክልል ወይም በተመሳሳይ ጊዜ የክልልና የፌደራል በሚሆንበት ጊዜ በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በይግባኝ የሚሰጥ ውሳኔ የመጨረሻ ውሳኔ አይደለም፡፡ የመጨረሻ የሚሆነው በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ከታየ በኋላ ነው፡፡ (አመልካች ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምዕራብ እና ጋምቤላ ሪጅን እና ተጠሪ ወ/ሮ ሳባ መንገሻ ሚያዝያ 21 ቀን 2006 ዓ.ም. ሰ/መ/ቁ 94102 ቅጽ 16 እንዲሁም (አመልካች መተሃራ ስኳር ፋብሪካ እና ተጠሪ እነ ጥበቡ እሸቱ (139 ሰዎች) መጋቢት 22 ቀን 2006 ዓ.ም. ሰ/መ/ቁ 94869 ቅጽ 16 ይመለከቷል፡፡) በሁለቱም መዝገቦች በክልል የታዩ የስራ ክርክሮች እንደ መጨረሻ ፍርድ ተቆጥረው በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሚታዩበት አግባብ በጭብጥነት ተይዞ እልባት አግኝቷል፡፡ በዚሁ መሰረት ከክልል መነሻ ያደረገ የስራ ክርክር በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት (ችሎቱ በክልሉ ከተደራጀ) ከመቅረቡ በፊት በቀጥታ ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ለመቅረብ ብቁ አይደለም፡
በሰ/መ/ቁ 94102 ክሱ መጀመሪያ የታየው በጅማ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ሲሆን ፍርድ ቤቱ በሰጠው ውሳኔ ላይ ተከሳሽ የነበረው አመልካች ለጅማ ዞን ከፍተኛው ፍርድ ቤት የይግባኝ አቤቱታ ያቀረበ ሲሆን አቤቱታው ተቀባይነት ሳያገኝ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ጸንቷል፡፡ በመቀጠል አመልካች በቀጥታ ለፌደራሉ ሰበር ሰሚ ችሎት የሰበር አቤቱታ አቅርቧል፡፡ ሆኖም ችሎቱ ጉዳዩ ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቀርቦ የመጨረሻ ውሳኔ ሳይሰጠው በቀጥታ ለፌደራል ሰበር ሰሚ ችሎት ለመቅረብ ብቁ እንዳልሆነ ገልጾ ውድቅ አድርጎታል፡፡
በሰ/መ/ቁ 94869 ጉዳዩ የተጀመረው በምስራቅ ኦሮሚያ አሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ሲሆን ቦርዱ ተጠሪዎችና ሌሎች ሠራተኞች ያቀረቡትን ክስ የከፊሎቹን ይርጋን መሰረት በማድረግ የቀሩትን ደግሞ ስልጣን የለኝም በማለት ውድቅ አድርጎታል፡፡ ተጠሪዎች በውሳኔው ቅር በመሰኘት ለክልሉ ጠቅለይ ፍርድ ቤት የይግባኝ አቤቱታ ያቀረቡ ሲሆን ፍርድ ቤቱም ቦርዱ የሰጠውን ብይን በመሻር በፍሬ ነገሩ ላይ ውሳኔ እንዲሰጥ መዝገቡን ለቦርዱ መልሶታል፡፡ አመልካች የሰበር አቤቱታ ያቀረበውም የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሰጠው ውሳኔ ላይ ነው፡፡ ሆኖም አመልካች ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሰበር አቤቱታ ሳያቀርብ ለፌደራሉ ሰበር ችሎት በቀጥታ የሰበር አቤቱታ ማቅረብ እንደማይችል ተገልጾ አቤቱታው ውድቅ ተደርጎበታል፡፡
በሁለቱም መዝገቦች ላይ የስራ ክርክር ከሌሎች ክርክሮች በተለየ የተከራካሪውን ወገን ማንነት ከግምት ውስጥ በማስገባት የክልልና የፌደራል ተብሎ ሊከፈል እንደማይገባና የክልል ፍርድ ቤቶች የስራ ክርክርን የሚያዩት በውክልና ስልጣናቸው እንዳልሆነ አቋም ተይዞበታል፡፡ ከዚህ አንጻር በሰ/መ/ቁ 94102 አመልካች የጅማ ዞን ከፍተኛው ፍርድ ቤት በሰጠው ውሳኔ ላይ ለክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት የሰበር አቤቱታ ሳያቀርብ በቀጥታ ለፌደራሉ ሰበር ችሎት የሰበር አቤቱታ ሊያቀርብ አይችልም፡፡
ተመሳሳይ የችሎቱ አቋም በሰ/መ/ቁ 94869 ላይም ተንጸባርቋል፡፡ ሆኖም የጉዳዩ መነሻ የክልሉ አሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ በመሆኑ የችሎቱ ውሳኔ ግልጽ ስህተት የተሰራበት እንጂ ህጉ በአግባቡ የተተረጎመበት አይደለም፡፡ በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁ 377/96 አንቀጽ 140(1) እና 154(1) ግልጽ ሆኖ እንደተደነገገው ከማናቸውም ቋሚ ወይም ጊዜያዊ ቦርድ የተሰጠ ውሳኔ ይግባኝ የሚቀርበው ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው፡፡ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የምስራቅ ኦሮሚያ አሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ የሰጠውን ውሳኔ በይግባኝ ያየውም በውክልና ስልጣኑ እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ ስለሆነም ይህ ጉዳይ በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በማናቸውም መልኩ ቢሆን ሊታይ አይችልም፡፡ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በይግባኝ አይቶ የመጨረሻ ውሳኔ የሰጠባቸው ጉዳዮችን የማየት ስልጣን የተሰጠው የፌደራሉ ሰበር ሰሚ ችሎት እንጂ የክልል ሰበር ሰሚ ችሎት እንዳልሆነ በአዋጅ ቁ 25/88 አንቀጽ 10(1) ተደንግጎ ይገኛል፡፡ ህጉ አሻሚነት የለውም፤ ግልጽ ነው፡፡ የችሎቱም ስህተት እንዲሁ ግልጽ ሆኖ ይታያል፡፡
በሰ/መ/ቁ 94102 እና 94869 ውሳኔ የተሰጠው በ2006 ዓ.ም. ሲሆን ከአምስት ዓመት በፊት በ2001 ዓ.ም. በሰ/መ/ቁ 37940 (አመልካች የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን እና ተጠሪ ተስፋዬ ፀጋዬ ጥር 28 ቀን 2001 ዓ.ም. ያልታተመ) ችሎቱ ያንጸባረቀው ከአቋም ከሁለቱ መዝገቦች ተቃራኒ ነው፡፡ በዚህ መዝገብ ላይ የጉዳዩ መነሻ ተጠሪ የስር ከሳሽ በመሆን በአርባ ምንጭ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ያቀረቡት ክስ ሲሆን ፍ/ቤቱ ክሳቸውን ውድቅ በማድረጉ ይግባኝ ለጋሞ አካባቢ ከፍተኛ ፍ/ቤት የይግባኝ አቤቱታ አቅርበው ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የስር ፍ/ቤትን ውሳኔ ሽሮታል፡፡ አመልካቹ የሰበር አቤቱታ ያቀረበው የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ ችሎቱም ለክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በቅድሚያ የሰበር አቤቱታ አልቀረበም በሚል የአመልካችን አቤቱታ ውድቅ አላደረገውም፡፡
ሶስት ዳኞች የተሰየሙበት የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር አጣሪ ችሎት በዋናው ሰበር ሰሚ ችሎት መጣራት ያለባቸውን ነጥቦች ለይቶ በሚሰጠው ትዕዛዝ የመጨረሻ ሊባል አይችልም፡፡ (አመልካች አቶ ኃይሉ ዴሬሳ እና ተጠሪ ወ/ሮ ሱፌ አለሙየካቲት 6 ቀን 2006 ዓ.ም. ሰ/መ/ቁ 90928 ቅጽ 15) በዚህ መዝገብ ላይ ከስር ፍርድ ቤት ጀምሮ ለክርክሩ መነሻ የነበሩት መኖሪያ ቤትና ሰርቪስ ቤት የጋራ ንብረት ናቸው በማለት ጉዳዩን በይግባኝ ባየው የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ በመሰጠቱ አመልካች በውሳኔው ቅር በመሰኘት ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሰበር አቤቱታ አቅርበዋል፡፡ የሰበር አጣሪ ችሎቱ አቤቱታውን መርምሮ ሰርቪስ ቤቶቹ የጋራ ናቸው የመባሉን አግባብነት ለማጣራት በሚል አቤቱታው ለሰበር ችሎቱ እንዲቀርብ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ አቤቱታው በክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት እየታየ እያለ አመልካች በዋናው መኖሪያ ቤት ላይ ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሰበር አቤቱታ አቅርበዋል፡፡ አቤቱታውን ሊያቀርቡ የቻሉትም አጣሪ ችሎቱ ሰርቪስ ቤቶቹን ብቻ በተመለከተ ያስቀርባል ማለቱ በዋናው ቤት ላይ ለክልሉ ሰበር ችሎት የቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት እንዳጣ ያስቆጥረዋል በማለት ነው፡፡
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የአመልካችን አቤቱታ ከመረመረ በኋላ አቤቱታው የመጨረሻ ፍርድ ባገኘ ጉዳይ ላይ የቀረበ ባለመሆኑ ለሰበር ለመቅረብ ብቁ አይደለም በማለት ውድቅ አድርጎታል፡፡ ለዚህም የተሰጠው ምክንያት በአጣሪ ችሎቱ የተሰጠው ትዕዛዝ ጊዜያዊ አገልግሎት ያለው ከመሆኑም በላይ አምስት ዳኞች የሚሰየሙበት የክልሉ ሰበር ችሎት በአጣሪ ችሎት በተያዘው ጭብጥ ላይ ሳይገደብ በሌሎች ነጥቦችም ላይ ጭብጥ በመመስረት ተገቢውን ውሳኜ መስጠት የሚችል በመሆኑ ነው፡፡
Public Servants’ Pension (Amendment) Proclamation No. 907-2015
Click HERE to download.
You can also get the file from the official website of Public Servant Social Security Agency
ተፈጻሚ ስለሚሆነው ህግ
የስራ መሪዎችን የስራ ሁኔታ የሚገዛ የስራ መሪዎች መተዳደሪያ ደንብ ካለ በስራ መሪውና በአሰሪው መካከል ያለው ግንነኙነት የሚመራው በዚሁ መተዳደሪያ ደንብ ነው፡፡ ይህን ነጥብ አስመልክቶ የሰበር ችሎት በሰ/መ/ቁ 60489 (አመልካች አቶ አምባዬ ወ/ማርያም እና ተጠሪ የኢትዮጵያ የእህል ንግድ ድርጅት ጥር 14 ቀን 2004 ዓ.ም. ቅጽ 13) የሚከተለውን ትርጉም ሰጥቷል፡፡
“በግራ ቀኙ መካከል ስራ ላይ ያለው ልዩ ህግ (የስራ መሪዎች መተዳደሪያ ደንብ) እስካለ ድረስ እና ያለው ደንብ ደግሞ ለሞራልና ለህግ ተቃራኒ ነው ወይም ተፈጻሚነት ሊኖረው የማይገባበትን ህጋዊ ምክንያት እስካልቀረበ ድረስ ተፈጻሚነት የሚኖረው ይሄው ልዩ ህግ በመሆኑ ወደ አጠቃላይ የፍታሐብሔር ድንጋጌዎች ተፈጻሚነት ያላቸውን የህግ ማዕቀፍ ፍለጋ የሚኬድበት አግባብ የለም፡፡”
የመተዳደሪያ ደንቡ በቀጥታ ሆነ በተዘዋዋሪ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 ተፈጻሚነት እንዲኖረው የሚፈቅድ ሲሆን አዋጁ በስራ መሪም ላይ ተፈጻሚነት ይኖረዋል፡፡ (አመልካች አቶ ዳዊት ሸዋቀና እና ተጠሪ ስኳር ኮርፖሬሽን መጋቢት 25 ቀን 2005 ዓ.ም. ሰ/መ/ቁ 84661 ቅጽ 15)
የስራ መሪ መታገድ እና ውጤቱ
የስራ መሪ ለተወሰነ ጊዜያት ከስራና ከደመወዝ ታግዶ መጨረሻ ላይ ቢሰናበት የታገደው ካለበቂ ምክንያት ቢሆንም እንኳን ለታገደበት ጊዜ ደመወዝ አይከፈለውም፡፡ (አመልካች ንብ ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር እና መልስ ሰጭ አቶ ተገኑ መሸሻ ሰ/መ/ቁ 18307 ጥቅምት 25 ቀን 1998 ዓ.ም ቅጽ 2) በዚሁ ጉዳይ ላይ የሰበር ችሎት ለውሳኔው መሰረት ያደረገው የፍ/ህ/ቁ 2541(1) ድንጋጌን ሲሆን ለድንጋጌው ትርጉም ከመስጠቱ በፊት የድንጋጌውን ይዘት እንደሚከተለው አስቀምጦታል፡፡
“…ሠራተኛው አንድም የስራ አገልግሎት ባይሰጥም እንኳን ይኸው ሁኔታ አሰሪው ስራ ሳይሰጠው በመቅረቱ ወይም እንዳይሰራ በመከልከሉ የተነሳ እንደሆነ ደመወዙን ለማግኘት መብት አለው…”
ምንም እንኳን የድንጋጌው መልእክት ግልፅ ቢሆንም ችሎቱ በፍ/ህ/ቁጥር 2541(1) የተቀመጠው ድንጋጌ የሚያገለግለው “የስራ መሪው የስራ ውሉ ባልታገደበት ወይም ባልተቋረጠበት ጊዜ ሥራ ላይ ሆኖ ነገር ግን አሰሪው ስራ ሳይሰጠው ወይም እንዳይሰራ በከለከለው ጊዜ ነው፡፡” በማለት ተርጉሞታል፡፡ በዚህም የተነሳ የፍ/ህ/ቁ 2541(1) የስራ መሪው ከስራና ከደመወዝ ታግዶ የስራ አገልግሎት ላልሰጠባቸው ጊዜያቶች ደመወዝ እንዲከፈለው የሚፈቅድ ድንጋጌ እንዳልሆነ ድምዳሜ ላይ ደርሷል፡፡
የዕገዳው ከፍተኛ ጊዜ በስራ መሪዎች መተዳደሪያ ደንብ በግልጽ ሰፍሮ እያለ አሰሪው በዚህ ጊዜ ውስጥ የዲሲፕሊን እርምጃ ካልወሰደ በደንቡ ላይ ከተቀመጠው የእገዳ ጊዜ በላይ ላሉት ጊዜያት አሰሪው ደመወዝ ለመክፈል ይገደዳል፡፡ በሰ/መ/ቁ 37982 (አመልካች የትምህርት መሣሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት እና ተጠሪ አቶ ታደሰ ዘነበ ሐምሌ 16 ቀን 2001 ዓ.ም. ቅጽ 8) የአመልካች ድርጅት የስራ መሪዎች መተዳደሪያ ደንብ በጥፋት ምክንያት አንድ የሥራ መሪ ታግዶ ሊቆይ የሚችለው ከአንድ ወር ላልበለጠ ጊዜ ሲሆን ተጠሪ የአንድ ወር ጊዜው ካበቀ በኋላ ለሰባት ወራት ከስራና ከደመወዝ በመታገዳቸው አመልካች የሰባት ወራት ደመወዝ ለተጠሪ የመክፍል ግዴታ እንዳለበት በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው የውሳኔ ክፍል በሰበር ችሎትም ጸንቷል፡፡
የስራ ውል መቋረጥ እና ውጤቱ
በስራ መሪነት ደረጃ ላይ በማገልገል ላይ ያለ ሰራተኛ ያለበቂ ምክንያት ቢሰናበት ኪሳራ ወይም ካሳ ከማግኘት ያለፈ መፍትሔ በህጉ ላይ አልተቀመጠለትም ፡፡ የስራ ውላቸው በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁ 377/96 ከሚመራ ሰራተኞች አንፃር ሲታይ የስራ ውል ከህግ ውጪ መቋረጥ በተመለከተ የስራ መሪ የሆነ ሰራተኛ በሁለት መልኩ ተጠቃሚ አይደለም ይህም
ሀ. ውዝፍ ደመወዝ አይከፈለውም
ለ. ወደ ስራ የመመለስ መብት የለውም
ወደ ስራ የመመለስ መብት
በውስጥ ደንብ በግልጽ ካልተመለከተ በስተቀር ከህግ ውጭ የተሰናበተ የስራ መሪ ወደ ስራ የመመለስ መብት የለውም
ፍርድ ቤት ከህግ ውጭ ከስራ የተሰናበተን የስራ መሪ ወደ ስራ እንዲመለስ ውሳኔ ሊሰጥ የሚችለው የስራ መሪዎችን በተመለከተ በአሰሪው መስሪያ ቤት የአስተዳደር የውስጥ መመሪያ ሲኖርና ይህ መመሪያ ከስርዓቱ ውጭ የተሰናበተ የስራ መሪ ወደ ስራው እንዲመለስ የሚፈቅድ ሲሆን ነው (አመልካች የአርሲ እርሸ ልማት ድርጅት እና ተጠሪ አቶ ሰለሞን አበበ ታህሳስ 10 ቀን 1998 ዓ.ም. ሰ/መ/ቁ 15815 ቅጽ 3)
የሰበር ችሎት በውሳኔው ላይ እንዳተተው ፍርድ ቤቶች የስራ መሪ ወደ ስራው እንዲመለስ ውሳኔ ከመስጠታቸው በፊት ለውሳኔያቸው መሰረት ያደረጉትንና ይህንኑ የሚቅድ የውስጥ ደንብ ስለመኖሩ በግልጽ ማመልከትና የደንቡን ድንጋጌ መጥቀስ ይኖርባቸዋል፡፡ ለውሳኔያቸው መነሻ የሚሆን ደንብ በሌለ ጊዜ ተፈጻሚ የሚሆነው ህግ የፍትሀ ብሔር ህግ ነው
በሰበር ውሳኔው ላይ እንደተመለከተው የስራ መሪ የስራ ውሉ ከህግ ውጭ ያለበቂ ምክንያት የተቋረጠ ቢሆንም እንኳን ካሳ ከማግኘት ባለፈ ወደ ስራ የመመለስ መብት አይኖረውም፡፡ በሰ/መ/ቁ 15815 ተጠሪ ወደ ስራ እንዲመለስ በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ ተሸሮ ማስጠንቀቂያ ስላልተሰጠው የሁለት ወር ደመወዝ እንዲሁም ስንብቱ በበቂ ምክንያት ያልተደገፈ በመሆኑ የሶስት ወር ደመወዙ በካሳ መልክ እንዲከፈለው ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡
የውስጥ መተዳደሪ ደንብ ወደ ስራ መመለስን የሚፈቅደ ሲሆን
የስራ መሪ በፍትሐብሔር ህጉ መሰረት ወደ ስራ የመመለስ መብት ባይኖረውም ከአሰሪው ጋር ያለውን ግንኙነት የሚገዛ መተዳደሪ ደንብ ወደ ስራ የመመለስ መብትን በግልፅ የሚፈቅድ ከሆነ ከህግ ውጭ የመሰናበቱ አንዱ ውጤት ወደ ስራ መመለስ ነው፡፡ (አመልካች የኢትዮጵያ ቴሌኮምኒኬሽ ኮፖሬሽን እና ተጠሪ እነ አቶ በቀለ ኩምሳ (3 ሰዎች) ጥቅምት 10 ቀን 2000 ዓ.ም. ሰ/መ/ቁ 21329 ቅጽ 6) በዚህ መዘገብ ጉዳዩ በተጀመረበት የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ አመልካች መልስ ሰጭዎችን ከተሰናበቱበት ጊዜ ጀምሮ ወደ ስራ እስከተመለሱበት ጊዜ ድረስ ያለውን ውዝፍ ደመወዝ ከፍሎ ወደ ስራ እንዲመልሳቸው ሲሆን ጉዳዩ በይግባኝ የቀረበለት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትም የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ጉድለት የለበትም በሚል ሳይቀበለው ቀርቷል፡፡
አመልካች በስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ቅር በመሰኘት የሰበር አቤቱታ ያቀረበ ሲሆን የክርክሩም ነጥብ ሁለቱም የውሳኔ ነጥቦች ማለትም ውዝፍ ደመወዝ እና ወደ ስራ መመለስን በተመለከተ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሟል በማለት ነው፡፡
ይሁን እንጂ በሰበር ያስቀርባል የተባለበት ነጥብ ወደ ስራ መመለስን በተመለከተ ሳይሆን ውዝፍ ደመወዝ ይከፈል በሚል በተሰጠው የውሳኔ ክፍል አግባብነት ለመመርመር ነው፡፡ ወደ ስራ መመለስን በተመለከተ ያስቀርባል ባለመባሉም የስር ፍርድ ቤቶች ይህን አስመልክቶ የሰጡት ውሳኔ መጽናቱ መገንዘብ ይቻላል፡፡
ካሳና ሌሎች ክፍያዎች
ከላይ በሰ/መ/ቁ 21329 የተገለፀው ሁኔታ የስራ መሪው ወደ ስራ እንዲመለስ ከተወሰነ በኃላ ሊከፈለው ስለሚገባ ክፍያ በተመለከተ ጥያቄ ያስነሳል፡፡ በዚሁ መዝገብ ላይ ተጠሪዎች ስራ ካቋረጡበት ጊዜ ጀምሮ ውዝፍ ደመወዝ እንዲከፈላቸው በመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የተወሰነ ሲሆን ይግባኝ የቀረበለት የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም የስር ፍ/ቤትን ውሳኔ አፅንቷል፡፡ የሰበር አቤቱታ የቀረበለት የሰበር ችሎት የስር ፍርድ ቤቶችን ውሳኔ ከሻረ በኃላ የስራ መሪ ከህግ ውጪ ቢሰናበትም ወደ ስራው ሲመለስ ውዝፍ ደመወዝ ሊከፈለው እንደማይገባ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡
ሰበር ለውሳኔው መሰረት ያደረገው የፍ/ህ/ቁ 2573 ድንጋጌ አፈፃፀምን አስመልክቶ በሰጠው ሀተታ በድንጋጌው መሰረት ካሳ የሚከፈለው ከስራ ለተሰናበተ (እንዲመለስ ላልተወሰነለት) የስራ መሪ እንጂ ወደስራው እንዲመለስ ተወስኖለት ወደስራ ለተመለሰ አይደለም፡፡ ከህግ ውጭ የተሰናበተ የስራ መሪ ወደ ስራ የማይመለስ ከሆነ በዋነኛነት በፍ/ህጉ አንቀጽ 2573 እና 2574(2) መሰረት ከሶስት ወር ደመወዙ የማይበልጥ ካሳ፤ በአንቀጽ 2570(2) መሰረት ከሁለት ወር የማይበልጥ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ እና በተለየ መልኩ ገደብ የሚያደርግ ሁኔታ ከሌለ በስተቀር ያልተጠቀመበት የዓመት እረፍት በሙሉ በገንዘብ ተቀይሮ ይከፈለዋል፡፡ (አመልካች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ተጠሪ አቶ አሰበወርቅ ዘገየ ታህሳስ 15 ቀን 2000 ዓ.ም. ሰ/መ/ቁ. 23609 ቅጽ 7)
በአንድ ውሳኔ ሁለት ጊዜ የፍርድ ባለዕዳ! (የሰበር መ/ቁ. 19205)
አመልካች አቶ ሽኩር ሲራጅ
መልስ ሰጪ አቶ ሙላት ካሣ
ሰ/መ/ቁ. 19205
መጋቢት 25/1999 ዓ.ም.
የሰበር ውሳኔዎች ቅጽ 4
ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ በፍርድ ቤት የተወሰነበትን ገንዘብ በአፈጻጸም እንዲከፍል አቤቱታ የቀረበበት የፍርድ ባለዕዳ እንደፍርዱ ሊፈጽም ባለመቻሉ ቤቱ ተሽጦ ለዕዳው መክፈያነት እንዲውል አፈጻጸሙን የሚያየው ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ይሰጣል፡፡ ሆኖም በትዕዛዙ መሰረት ቤቱ ከመሸጡ በፊት የፍርድ ባለዕዳው 20,000 ብር (ብር ሃያ ሺ) በሞዴል 85 ያስይዛል፡፡ በመቀጠል የፍርድ ባለመብቱ በሞዴል 85 የተያዘው ገንዘብ እንዲለቀቅለት ለፍርድ ቤቱ አመለከተ፡፡
ገንዘብ በሞዴል 85 ከተያዘ በኋላ አፈጻጸም ቀላልና ያለቀለት ጉዳይ ቢሆንም የፍርድ ባለመብት ባቀረበው አቤቱታ መሰረት የተያዘውን ገንዘብ ማግኘት አልቻለም፡፡ ምን ተፈጠረ? መጀመሪያ አፈጻጸም የተከፈተበት መዝገብ ጠፋ ተባለ፡፡ ተባለ ብቻ ሳይሆን በቃ ጠፋ! በመዝገብ መጥፋት የትኛውም ፍርድ ቤት ቢሆን ስሙ መነሳት ባይኖርበትም መልካም የፍርድ ቤት አስተዳደር ባለበት ፍርድ ቤት ውስጥ እንኳን ሳይቀር የመዝገብ መጥፋት አንዳንዴ ይከሰታል፡፡ ደግነቱ የጠፋው መዝገብ የአፈጻጸም በመሆኑ ሌላ የአፈጻጸም መዝገብ መክፈት የሚቻል በመሆኑ በፍርድ ባለመብት ላይ ከሚያስከትለው አላስፈላጊ ወጪና መጉላላት በቀር የከፋና የማይመለስ ጉዳት የማድረስ ውጤት የለውም፡፡ እናም በዚህኛው በጠፋው የአፈጻጸም መዝገብ ምትክ በፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንት ትዕዛዝ ሌላ የአፈጻጸም መዝገብ እንዲከፈት ተደረገ፡፡
ሆኖም ነገሩ በዚህ አላበቃም፡፡ የመዝገቡ መጥፋት ሳያንስ ሌላ ጉድ የሚያሰኝ ነገር ተከሰተ፡፡ በሞዴል 85 የተያዘው ገንዘብ ጠፋ!! አዲስ በተከፈተው መዝገብ ላይ ፍርድ ቤቱ የተያዘው ገንዛብ ወጪ ሆኖ ለፍርድ ባለመብት እንዲከፈል ትዕዛዝ ሲሰጥ ትዕዛዙ የደረሰው የፋይናንስ ቢሮ በሞዴል 85 ተይዞ የነበረው ገንዘብ ፍርድ ቤቱ ራሱ በ5/5/89 ዓ.ም. በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ገንዘቡ አቶ ኤልያስ አርአያ ለተባለ ግለሰብ መከፈሉን በመግለፁ ነገሩ ሁሉ “ፍጥጥ ቁልጭ” ሆነ፡፡
እንግዲህ ያለው መፍትሄ ምንድነው? በአንድ በኩል የፍርድ ባለመብት መብቱን በህግ ሀይል ለማስከበር ክስ አቅርቦ ተከራክሮ አሸንፎ ተፈርዶለት የፍርዱን ፍሬ በአፈጻጸም እንዲከፈለው ከችሎቱ ፊት ቆሟል፡፡ በሌላ በኩል የፍርድ ባለዕዳው መጀመሪያ በቀረበበት ክስ በመረታቱ እንደ ፍርዱ ፈጽም ሲባል የሚፈለግበትን ገንዘብ በተለመደው ህጋዊ ስነ ስርዓት መሰረት ‘አድርግ!’ እንደተባለው ገንዘቡን በሞዴል 85 ገቢ አድርጓል፡፡ የፍርድ ባለዕዳ ሆነ የፍርድ ባለገንዘብ በዚህ መዝገብ ላይ በተፈጠረው አሳዛኝ አጋጣሚ ስህተትም ሆነ ጥፋት የለባቸውም፡፡ ጥፋቱ ግራ ቀኙን አይቶ ፍትህ በሚያጎናጽፈውና ዳኝነት የሚሰጠው የራሱ የፍርድ ቤቱ እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡
በመጨረሻ ወደ ሰበር ያመራው ጉዳይ አመጣጥና የታሪኩ መነሻ ከላይ የተገለጸው ሲሆን የተፈጠረው ክስተት ጉዳዩን ትኩረት የሚስብ አድርጎታል፡፡ የበለጠ ትኩረትን የሚስበው ግን ክስተቱ ሳይሆን ለክስተቱ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትን ጨምሮ በየደረጃው ጉዳዩ የቀረበላቸው ፍርድ ቤቶች መፍትሄ ይሆናል በሚል የሰጡት ትዕዛዝ እና ውሳኔ ነው፡፡
በመጀመሪያ በሞዴል 85 የተያዘው ገንዘብ ለሌላ ሰው መከፈሉን ያወቀው አፈጻጸሙን የያዘው ፍርድ ቤት “የፍርድ ባለዕዳ ገንዘቡን በፍርድ ቤት ካስያዘ በፍርድ ቤት እንደተቀመጠ ስለሚቆጠር የፍርድ ባለመብት ጉዳዩን ተከታትሎ ገንዘቡ ለሌላ 3ኛ ወገን እንዲከፈል ምክንያት የሆነውን አካል ጠይቆ ገንዘቡን ከሚቀበል በቀር ከፍርድ ባለዕዳ ድጋሚ መጠየቅ አይችልም” በማለት ወሰነ፡፡ ይህ ውሳኔ በይግባኝ በከፍተኛው ፍርድ ቤት የተሻረ ሲሆን የከፍተኛው ፍርድ ቤትን ውሳኔ የጠቅላይ ፍርድ ቤት መልሶ ሽሮታል፡፡ ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ሲሽር የሰጠው ምክንያት “የፍርድ ባለዕዳ በሞዴል 85 ያስያዘውን ገንዘብ በፍትሃብሄር ስነ ስርዓት ህግ ቁ. 395 መሰረት እንደተከፈል ይቆጠራል” የሚል ሲሆን በይዘቱ አፈጻጸሙን የያዘው ፍርድ ቤት ከሰጠው ውሳኔ ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡
እንዲህ እንዲህ እያለ በመጨረሻ ጉዳዩ ሰበር ደረሰ፡፡ የሰበር ችሎት የግራ ቀኙን ክርክርና የስር ፍርድ ቤቶችን ውሳኔዎች ከመረመረ በኋላ የሚከተለውን ጭብጥ በመያዝ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ ሰበር ችሎቱ ምላሽ ያሻዋል በሚል የያዘው ጭብጥ “በሞዴል 85 ተይዞ የነበረው ገንዘብ ለሌላ 3ኛ ወገን ቢከፈልም ለአሁን አመልካች እንደተከፈለ መቆጠሩ አግባብ ነው ወይስ አይደለም?” የሚል ነው፡፡ ችሎቱ ለተያዘው ጭብጥ ምላሽ ለመስጠት የራሱን ትንተና ከሰጠ በኋላ በመጨረሻ ላይ የደረሰበት ድምዳሜ የሚከተለው ነበር፡፡
“በፍርድ ቤት ገንዘብ ገቢ በማድረግ እዳ መክፈል አንድ አማራጭ መንገድ ቢሆንም የፍርድ ባለእዳው እዳውን ጨርሷል መባል ያለበት ይህ ሂደት ተጠናቆ የፍርድ ባለመብቱ ገንዘቡን ሲረከብ ሊሆን ይገባል፡፡”
ሰበር ችሎቱ ይህን አቋሙን ሲያጠናክር በተጨማሪነት እንዲህ ብሎ ነበር፡፡
“የፍርድ ባለመብቱ ገንዘቡን ባልተረከበበት ሁኔታ የፍርድ ባለዕዳው እንደከፈለ መቁጠሩ አግባብ አይደለም፡፡ የፍርድ ባለዕዳው ያስያዘው ገንዘብ ፍርዱ ከመፈጸመ በፊት ተመልሶ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ከተከፈለ ባለዕዳው ገንዘብ እንዳስያዘ ሊቆጠር አይገባውም፡፡ ያስያዘው ገንዘብ ሳይኖር በፍትሃብሔር ስነ ስርዓት ህግ ቁጥር 395(2) መሰረት ፍርዱ እንደተፈጸመ ሊቆጠር አይገባውም፡፡”
በዚሁ መሰረት የሰበር ችሎቱ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ ሽሮ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትን ውሳኔ በማጽናት የፍርድ ባለዕዳው ለብር 20,000 (ሃያ ሺ ብር) ተጠያቂ ነው የሚል ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ ለመሆኑ በሞዴል 85 የተያዘው ገንዘብ እንዴት ለሌላ ግለሰብ ሊከፈል ቻለ? ለዚህ ጥያቄ በሰበር ችሎቱ ምላሽ ለመስጠት ተሞክሯል፡፡ ሰበር ችሎቱ በዚህ ረገድ በውሳኔው ላይ እንዳሰፈረው በሞዴል 85 ተይዞ የነበረውን ገንዘብ ወሰደ የተባለው ግለሰብ በምን ምክንያት እንደወሰደ የተገለጸ ነገር የለም፡፡ ይሁን እንጂ ገንዘቡ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንደተለቀቀለት ችሎቱ ከፍርድ ቤቶቹ መዝገብ እንደተረዳ ሳይጠቁም አላለፈም፡፡ በዚህ መልኩ የተገለጸውና ያልተገለጸው ከተለየ በኋላ ከሁለቱ ውጪ የሆነ ሌላ ፍሬ ነገር ደግሞ በራሱ በችሎቱ ታከለበት፤ እንዲህ የሚል፡፡
“…ይህ ገንዘብ ለአሁን መልስ ሰጪ እዳ መክፈያ ውሎ ሊሆን እንደሚችልም ይገመታል”
ግምት ነው እንግዲህ!
ሲጠቃለል በፍርድ ቤት ትዕዛዝ፤ በፍርድ ቤት ስህተት፤ በፍርድ ቤት ጥፋት ለተከፈለው ገንዘብ ተጠያቂ ነህ የተባለው ፍርድ ቤቱ ሳይሆን የፍርድ ባለዕዳው ነው፡፡ የሰበር ችሎትን ጨምሮ በየደረጃው ጉዳዩን ያዩት ፍርድ ቤቶች በፍትሃብሄር ስነ ስርዓት ህግ ቁ. 395 የህግ ትርጉም ላይ በመሽከርከር ከመሰረታዊው ጥያቄ (በሚያስተዛዝብ መልኩ) ሸሽተዋል፡፡ ፍርድ ቤት የሰው ገንዘብ አላግባብ ለማይገባው ሰው ከከፈለ ዋነኛ እና ብቸኛ ተጠያቂውም ፍርድ ቤት እንጂ የፍ/ባለመብት ሆነ የፍ/ባለዕዳ አይደሉም፡፡
ለመሆኑ የትኛው ይሻል ነበር? ፍርድ ቤቱን ከሃያ ሺ ብር ተጠያቂነት ከለላ መስጠት ወይስ ለፍርድ ቤት ተዓማኒነትና ፍትሐዊነት ዘብ መቆም? ሲሆን ሲሆን መዝገብ ጠፍቶ እያለ፤ በሞዴል 85 የተያዘ ገንዘብ ጠፍቶ እያለ ይህን ጉድ አገር ሳይሰማው በአስተዳደራዊ መንገድ ፍርድ ቤቱ በራሱ አነሳሽነት ከራሱ በጀት ቀንሶ ጠፋ የተባለውን ገንዘብ መተካት ይጠበቅበት ነበር:: እንግዲህ በሞዴል 85 ገንዘብ የሚያስይዝ የፍርድ ባለዕዳ ዋስትናው ምን ይሆን? ችሎቱ ይህ ጥያቄ አላሳሰበውም፡፡ ሆኖም ከፍርድ ቤት ፍትሐዊና ተዓማኒነት ያለው አገልግሎት ለሚጠብቀው ዜጋ ሁሉ እጅግ አሳሳቢ ነው፡፡
AND THANKS TO:
10,020 Subscribers
900,000 plus visitors who have visited my blog more than 3 million times
Submitted 2,717 comments
and shared blog post on social media sites 20,704 times
የሰ/መ/ቁ 100079 “ን” አንብበን ስናበቃ ለተፈጥሮ ሰው ብቻ የምንጠቀምባቸው የተለመዱ አባባሎች ለህግ ሰውም ሊውሉ የመቻላቸው አጋጣሚ ሊኖር እንደሚችል እንረዳለን፡፡ በውሳኔው ላይ እንደተመለከተው አንድ የህግ ሰውነት ያለው ድርጅት በህጉ አግባብ ሳይፈርስና ህልውናውን ሳያጣ “በቁሙ ሊከስም” ይችላል፡፡ የዚህ አባባል ምንጩ በውሳኔው ላይ ባይገለጽም “በቁም መሞት” ከሚለው ሰውኛ አባባል እንደተቀዳ ያስታውቃል፡፡ አንዳንድ ጊዜ አንዳንድ ሰው ጊዜ ይጥለውና ከሰውነት ተራ ወጥቶ በቁሙ ይሞታል፡፡ አንዳንድ ጊዜ አንዳንድ ድርጅትም ማን እንደሚጥለው ባይታወቅም “ከህጋዊ ሰውነት ተራ ወጥቶ” በቁሙ ይከስማል፡፡ ድርጅት እንዲህ ሰውኛ ባህርይ የሚጋራ ከሆነ መሰል ሰውኛ አባባሎች ለድርጅት የሚውሉበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም፡፡ ለምሳሌ…ለሕጋዊ ሰውነት መድሀኒቱ ሕጋዊ ሰውነት ነው! ለድርጅት መክሰም አነሰው! ሕጋዊ ሰውነትን ማመን ቀብሮ ነው እና የመሳሰሉት የሕጋዊ ሰውነት አባባሎች ሆነው በቅርቡ ዕውቅና ማግኘታቸው አይቀርም፡፡
በሰ/መ/ቁ 10009 ህጋዊ ሰውነቱን ሳያጣ “በቁሙ የከሰመው” ድርጅት ሜጋ የኪነ ጥበብ ማዕከል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማሕበር ሲሆን ከመክሰሙ በተጨማሪ ሰውኛ ገጽታው በመጥሪያ አደራረስም ተንጸባርቋል፡፡ ክሱ በቀረበበት ፍ/ቤት ድርጅቱ 1ኛ ተከሳሽ የነበረ ሲሆን ክሱ በሚሰማበት ወቅት የወንጀሉ ክስና መጥሪያ አልደረሰውም፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት በሰበር ውሳኔው ላይ እንደተመለከተው ከሳሽ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን “የወንጀል ክሱንና መጥሪያውን ለማድረስ ጥረት አድርጎ ሊያገኘው ባለመቻሉ” ምክንያት ነው፡፡ ምናልባት መጥሪያ እንዳይደርሰው “ሆነ ብሎ እየተሸሸገ” ይሆን?
ገራሚውና አስገራሚው ነገር ድርጅቱ በቁሙ መክሰሙ አሊያም መጥሪያ እንዳይደርሰው መሰወሩ አይደለም፡፡ በሰበር ውሳኔው ላይ የሰፈረው የክርክሩ ሂደት እንደሚያሳየው ድርጅቱ በጋዜጣ አልተጠራም፡፡ ጉዳዩ በሌለበት እንዲታይም ትዕዛዝ አልተሰጠም፡፡ ሆኖም ግን በስር 2ኛ ተሳሳሽ (በሰበር መዝገቡ ላይ አመልካች) ከነበሩት የድርጅቱ የቀድሞ ስራ አስኪያጅ ጋር ጥፋተኛ ተብሏል፡፡ አመልካች ለሰበር ችሎት ባቀረቡት አቤቱታ ላይ ድርጅቱ በህጉ አግባብ ተጠርቶ ቀርቦ ሳይከራከር እንዲሁም በጋዜጣ ተጠርቶ ጉዳዩ በሌለበት እንዲታይ ትዕዛዝ ሳይሰጥና በዚሁ መሰረት ጥፋተኛ ሳይባል አመልካች ጥፋተኛ ሊባሉ እንደማይገባ በመግለጽ አጥብቀው ተከራክረዋል፡፡ ሆኖም የሰበር ችሎት በስር ፍ/ቤት ውሳኔ ላይ የሚገኘውን የሚከተለውን ሐተታ በመጥቀስ ድርጅቱ ጥፋተኛ እንደተባለ በደረሰበት ድምዳሜ መሰረት ክርክሩን ውድቅ አድርጎታል፡፡ ድርጅቱ ጥፋተኛ የተባለበት የስር ፍ/ቤት የውሳኔ ክፍል እንደሚከተለው ይነበባል፡፡
ስለሆነም ተከሳሹ የዐቃቤ ሕግን ማስረጃ የሚያስተባብል ማስረጃ ያላቀረቡ በመሆኑ በ1997ዓ.ም 1ኛ ተከሳሽ ባከናወነው የንግድ እቅስቃሴ ገቢን አሳውቆ ባለመክፈልና ተከሳሾች አሳሳች መረጃ በመስጠትና ኪሳራ ሪፖርት በማድረግና ከ1996ዓ.ም እስከ 2002 ዓ.ም ድረስ የተሰበሰበውን የተጨማሪ እሴት ታክስ የሰበሰቡትን በሙሉ ሪፖርት ባለማድረጋቸው ሁለተኛው ተከሳሽ (አመልካች) በስራ አስኪያጅነታቸው አንደኛ ተከሳሽ ለፈጸመው ድርጊት ተጠያቂ በመሆናቸው ተከሳሾች በአዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀጽ 96 እና አንቀጽ 97 ንዑስ አንቀጽ 3 (ሀ) አንደዚሁም በአዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀጽ 49 ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ ጥፋተኛ ናቸው’’
በእርግጥ ጥፋተኛ የሚል ቃል በውሳኔው ላይ የተጠቀሰ ቢሆንም ድርጅቱ ቀርቦ ሳይከራከር ብሎም ጉዳዩ በሌለበት እንዲታይ ትዕዛዝ ሳይሰጥ ውጤት ያለው የጥፋተኝነት ውሳኔ ሊሰጥ አይችልም፡፡ ምክንያቱም….በአጭሩ አያስኬድም፡፡ የጥፋተኝነት ውሳኔው ጸንቶ የሚቆምበት የህግ መሰረት የለውም፡፡ ከድርጅቱ ጥፋተኝነት ጋር ተያያዞ የተነሳውን ጭብጥ የበለጠ አስገራሚ የሚያደርገው ሌላም ነገር አለ፡፡ አመልካች ድርጅቱ ጥፋተኛ አይደለም በማለት በሰበር ችሎት ሽንጣቸውን ገትረው ሲከራከሩ የነበረው ለድርጅቱ በመቆርቆር አይደለም፡፡ የድርጅቱ ጥፋተኝነት ጭብጥ ሆኖ የተነሳው ድርጅቱ ጥፋተኛ ባልተባለበት የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ (አመልካች) ጥፋተኛ ልባል አይገባም በማለት ክርክር በማቅረባቸው ነው፡፡ ይህ ጭብጥ ሊፈታ የሚችለው አንድም ድርጅቱ ጥፋተኛ ባይባልም አመልካች እንደ ስራ አስኪያጅነታቸው ጥፋተኛ የሚባሉበት የህግ አግባብ እንዳለ አቋም በመያዝ አሊያም በህጉ አግባብ በድርጅቱ ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ ተሰጥቷል ሊባል እንደማይገባ/እንደሚገባ ጭብጥ መስርቶ ለዚሁ ጭብጥ ተገቢውን ምላሽ በመስጠት ነው፡፡ ከዚህ በተቃራኒው አመልካች ስለድርጅቱ ጥፋተኝነት አያገባቸውም፤ ስለ ድርጅቱ ለመከራከርም ውክልና የላቸውም የሚባል ከሆነ ግን ከመሰረታዊው ጭብጥ መራቅ ነው የሚሆነው፡፡ ይህን አስመልክቶ የችሎቱ ሐተታ እንደሚከተለው ይነበባል፡፡
“አመልካች ከ2003ዓ.ም ጀምሮ የአንደኛ ተከሳሽ ስራ አስኪያጅ እንዳልሆነና አንደኛ ተከሳሽንም ወክሎ ክርክር ለማቅረብ እንደማይችል በስር ፍርድ ቤት የገለጸ መሆኑን ግራ ቀኙ ካቀረቡት ክርክር ተገንዝበናል፡፡ አንደኛ ተከሳሽ የወንጀል ጉዳይ የታየው የወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዐት ሕግ አንቀጽ 162 አንቀጽ 167 እና ሌሎች ድንጋጌዎች ከሚደነግጉት ውጭ ነው ብሎ ካለ የስር ፍርድ ቤት አንደኛ ተከሳሽ በሌለበት አይቶ የሰጠው ፍርድ እንዲነሳለት ከሚያመለክት በስተቀር አንደኛ ተከሳሽ በሌለበት ታይቶ መወሰኑን አመልካች መከራከሪያ አድርጎ ሊያቀርብ የሚችል አይደለም፡፡ አንደኛ ተከሳሽ በመወከልም አንደኛ ተከሳሽ በሌለበት ታይቶ የተሰጠው ፍርድ እንዲነሳ ለመከራከር የሚያስችለው ውክልና ወይም ስልጣን የለውም ስልጣንም ቢኖረው ክርክሩ መቅረብ የሚገባው በወንጀለኛ መቅጫ ስነ-ስርዓት ሕግ ከአንቀጽ 197 እስከ አንቀጽ 102 የተደነገጉትን ድንጋጌዎች መሰረት በማድረግ መሆን የሚገባው በመሆኑ አመልካች ያቀረበው ክርክር የሕግ መሰረት ያለው ሆኖ አላገኘነውም፡፡”
የሰ/መ/ቁ 100079 ከላይ በቅንጭቡ ከቀረበው በላይ በርካታ ዘርፈ ብዙ የህግ ጥያቄዎችን ያስነሳል፡፡ አንባቢ በራሱ ይመዝነው ዘንድ የፍርዱ ሙሉ ይዘት እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡ ከዚያ በፊት ግን በተለየው ሓሳብ ላይ የሰፈረው የሚከተለው ቁም ነገር እንደ መንደርደሪያ ይሁን፡፡
ሕግና ሥርዓት ባለበት አገር አንደኛ ተከሳሽ የነበረው ድርጅት በእርግጥ ሕጋዊ ሰውነት ያለው ህያው ድርጅት ከሆነ ከሚመለከታቸው አካላት በማጣራት እውነት የማፈላላግ ሥራ መከናወን ነበረበት፡፡ በሌላ በኩል ድርጅቱ ሜጋ ማስታወቂያ ከተባለው ድርጅት ከተዋሃዳ የተቀለቀለ / Amalgamation merge /ስለመሆኑ በክርክር ሂደት ተነስቷል፡፡ ይህ በተመለከተም ሁለቱም ድርጅቶች ተዋህደው ከሆነ መቼ እና በማን ውሳኔ ሰጪነት ተዋሀዱ የሚለው መጣራት ነበረበት፡፡
የአንድ ድርጅት ሥራአስኪያጅ ኃላፊ የሚሆነው ድርጅቱ በሕግ አግባብ ጥፋተኝነቱ ሲረጋገጥ ብቻ ነው፡፡ …ድርጁቱ በህግ አግባብ መጥሪያ የደረሰው ስለመሆኑ አልተረጋገጠም፡፡ የአሁኑ አመልካችም ድርጅቱ ከለቀቁ ከአንድ ዓመት በኃላ ክስ የተመሰረተባቸው ስለመሆኑ እየተከራከሩ ነው፡፡ የስር ፍርድ ቤቶች የአሁኑ አመልካች ጥፋተኛ ከተባሉ ድርጅቱም ጥፋተኛ ነው በሚል ድምዳሜ ላይ መድረሳቸው ከውሳኔያቸው ይዘት መረዳት ይቻላል፡፡ ይሁንና የስር ፍርድ ቤቶች ድምዳሜ የህግ መሰረት ያለው አይደለም፡፡……..ቅድሚያ መረጋገጥ ያለበት የድርጅት ጥፋት መኖር ያለመኖር ነው፡፡ አንድ ድርጅት ጥፋተኛ ነው ወይስ አይደለም ወደ ሚለው ድምዳሜ ለመድረስም በህጉ የተዘረጋው የሙግት አመራር ሥርዓት በጥብቅ [ተግባራዊ] መደረግ ነበረበት፡፡ የስር ፍርድ ቤቶች አንደኛ ተከሳሽ የነበረው ድርጅት ሕጋዊ ሰውነት ያለውና ያልከሰመ መሆን ያለመሆኑን በአግባቡ ሳያጣሩ ጥሪ ቢደረግለትም አይቀርብም በሚል ሰበብ እውነት [የማፈላለግ] ግዴታቸው (truth finding) ወደ ጎን በመተው [ሕጉ] [የዘረጋውን] የሙግት አመራር ሥርዓት ሳይከተሉ ከውሳኔ ላይ መድረሳቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት መፈጸማቸውን የሚያሳይ ነው፡፡”
የሰ/መ/ቁ 100079
መጋቢት 4 ቀን 2007 ዓ/ም
ዳኞች፡- አልማው ወሌ
ዓሊ መሐመድ
ሡልጣን አባተማም
ሙስጠፋ አህመድ
ተኽሊት ይመሰል
አመልካች፡- አቶ ዕቁባይ በርሀ ገ/እግዚአብሔር – ጠበቃ ደሳለኝ መስፍን ቀረቡ
ተጠሪ፡- የኢትዮጵያ ገቢዎች ጉምሩክ ባለሥልጣን – ዐ/ህግ ወንድዬ ብርሃኑ ቀረቡ
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል
ፍ ር ድ
ጉዳዩ የቀረበው አመልካች የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 176025 ታህሳስ 19/2005 ዓ/ም የሰጠው ፍርድና የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የመዝገብ ቁጥር 131320 ጥር 21 ቀን 2006 ዓ/ም የሰጠው ፍርድ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታርምልኝ በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው ጉዳዩ ተጠሪ አመልካች የአንድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሥራ አስኪያጅ ሆኖ ሲሰራ ለግብር ስብሳበው መሥሪያ ቤት አሳሳች ማስረጃ የማቅረብና ተጨማሪ እሴት ታክስ የማሳወቅና የመክፈል ኃላፊነቱን ባለመወጠት ወንጀል ፈፅሟል በማለት ያቀረበውን ክስና ክርክር የሚመለከት ነው፡፡ በሥር ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሳሽ አመልካች ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡
14.የስር ፍርድ ቤት አንደኛ ተከሳሽ ከክርክሩ ውጭ እንዲሆን አላደረገም፡፡ የስር ፍርድ ቤት ተጠሪ በአንደኛ ተከሳሽ ላይ እና በአመልካች ላይ የቀረበውን የወንጀል ክስ እና ማስረጃ ከሰማና የአመልካችን መከላከያ ከመረመረ በኋላ ‘’ስለሆነም ተከሳሹ የዐቃቤ ሕግን ማስረጃ የሚያስተባብል ማስረጃ ያላቀረቡ በመሆኑ በ1997ዓ.ም 1ኛ ተከሳሽ ባከናወነው የንግድ እቅስቃሴ ገቢን አሳውቆ ባለመክፈልና ተከሳሾች አሳሳች መረጃ በመስጠትና ኪሳራ ሪፖርት በማድረግና ከ1996ዓ.ም እስከ 2002 ዓ.ም ድረስ የተሰበሰበውን የተጨማሪ እሴት ታክስ የሰበሰቡትን በሙሉ ሪፖርት ባለማድረጋቸው ሁለተኛው ተከሳሽ (አመልካች) በስራ አስኪያጅነታቸው አንደኛ ተከሳሽ ለፈጸመው ድርጊት ተጠያቂ በመሆናቸው ተከሳሾች በአዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀጽ 96 እና አንቀጽ 97 ንዑስ አንቀጽ 3 (ሀ) አንደዚሁም በአዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀጽ 49 ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ ጥፋተኛ ናቸው’’ በማለት ውሳኔ እንደሰጠ ከስር ፍርድ ቤት ከሰጠው ፍርድ በስምንተኛው ገጽ በአራተኛው ፓራግራፍ በግልጽ ሰፍሯል፡፡
ው ሳ ኔ
1.የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የፌዴረል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት የጥፋተኝነትና የቅጣት ውሳኔ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 195 ንዑስ አንቀጽ 2(ለ)2 መሰረት በድምጽ ብልጫ ጸንቷል፡፡
2.መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡
የማይነበብ የአራት ዳኞች ፊርማ አለበት
የልዩነት ሐሳብ
እኔ ስሜ በተራ ቁጥር አምስት የተሰየምኩት ዳኛ አብላጫው ድምጽ ከሰጠው ውሳኔ ባለመስማማት የሚከተለው የልዩነት ሐሳብ አስፍሬአለሁ፡፡
ጉዳዩ የተጀመረው በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን የአሁኑ ተጠሪ አንደኛ ተከሳሽ ሜጋ ኪነጥበብ ማዕካል ኃ/የተ/የግል ማህበር 2ኛ ተከሳሽ የአሁኑ አመልካች በማድረግ ስድስት ክሶች ያቀረበ ሲሆን በአመልካች ላይ ያቀረበው ክስ ገቢን አለማሳወቅ፣ ትርፍ አሳውቆ አለመክፈል፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ አለመክፈል የሚሉ ናቸው፡፡ አመልካች ድርጊቱን ክደው በመከራከራቸው የግራ ቀኙ ማስረጃዎች ተሰምተው ጥፋተኛ ተብሎው የእስራት ቅጣት ተወስኖ የተገደበላቸው ስለመሆኑ ከሥር ፍርድ ቤት መዝገብ መረዳት ይቻላል፡፡ አመልካች በየደረጃው ጉዳዩን በተመለከቱት ፍርድ ቤቶች ያቀረቡት ቅሬታ መሠረታዊ ይዘት በሥር ፍርድ ቤት አንደኛ ተከሳሽ የነበረው ጥፋተኛ ሳይባል መቀጣታቸው መሠረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት መሆኑ የሚያሰይ ነው፡፡ የአሁኑ ተጠሪ አንደኛ ተከሳሽ ጥፋተኛ እንደተባለ እና ስለ መፍረሱ የቀረበ ማስረጃ አለመኖሩን አመልካች ድርጁቱ ወክለው ባይከራከሩም ለምስክሮች መስቀለኛ ጥያቄ በማቅረብ የተከራከሩ በመሆኑ የተጣበበ መብት የለም የሚል ነው፡፡
በሥር ፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አንደኛ ተከሳሽ የነበረው ሜጋ ኪነጥበብ መእከል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ቀርቦ እንዲከራከር በሕጉ አግባብ ጥሪ የተደረገለት ስለመሆኑ ጉዳዩም በሌለበት እንዲታይ ግልጽ ትዕዛዝ የተሰጠ ስለመሆኑ የወሳኔው ይዘት አያሳይም ፡፡
ጉዳዩ በይግባኝ ሥልጣኑ የተመለከተው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሥር ፍርድ ቤት አንደኛ ተከሳሽ የነበረው የሜጋ ኪነጥበባት ማዕከል በሕጉ አግባብ እንዳልተጠራ በዚህ ምክንያት መዝገቡ ወደ ሥር ፍርድ ቤት መመለሱ ውጤት እንደሌለው በመግለጹ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ አጽሕጋዊ ሰውነት ያለቸው ድርጅቶች በሕግ በግልጽ በተመለከተ ጊዜ የወንጀል ተጠያቂነት ያለባቸው ስለመሆኑ በኢ.ፌ.ዲ.ሬ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 34 ተመልክቷል፡፡ የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀጽ 102 እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285 /1994 አንቀጽ 56(1) እንደተመለከተው ሕጋዊ ሰውነት ያለው ድርጅት የወንጀል ጥፋት ከፈፀመ የድርጅቱ ስራአስኪያጅ ተጠያቂ እንደሚሆን ተደንግጓአል፡፡ የዚህ ድንጋጌ የእንግልዝኛ ትርጉም “subject to sub-Article (3) where an entity commits an offence every person who is manager of that entity at that time is treated as having committed the offence and is liable penalty under this proclamation“ የሚል ነው፡፡ ከዚህ የህግ ድንጋጌ መሠረታዊ ይዘት ዓላማና መንፈስ መረዳት የሚቻለው የአንድ ድርጅት ሥራአስኪያጅ ኃላፊ የሚሆነው ድርጅቱ በሕግ አግባብ ጥፋተኝነቱ ሲረጋገጥ ብቻ ነው፡፡ ወደ ተያዘው ጉዳይ ሲንመጣ ድርጁቱ በህግ አግባብ መጥሪያ የደረሰው ስለመሆኑ አልተረጋገጠም፡፡ የአሁኑ አመልካችም ድርጅቱ ከለቀቁ ከአንድ ዓመት በኃላ ክስ የተመሰረተባቸው ስለመሆኑ እየተከራከሩ ነው፡፡ የስር ፍርድ ቤቶች የአሁኑ አመልካች ጥፋተኛ ከተባሉ ድርጅቱም ጥፋተኛ ነው በሚል ድምዳሜ ላይ መድረሳቸው ከውሳኔያቸው ይዘት መረዳት ይቻላል፡፡ ይሁንና የስር ፍርድ ቤቶች ድምዳሜ የህግ መሰረት ያለው አይደለም፡፡ ሕግ አውጪው ከላይ በጠቀሱኩዋቸው አዋጆች ላይ በግልጽ እንዳመለከተው ቅድሚያ መረጋገጥ ያለበት የድርጅት ጥፋት መኖር ያለመኖር ነው፡፡ አንድ ድርጅት ጥፋተኛ ነው ወይስ አይደለም ወደ ሚለው ድምዳሜ ለመድረስም በህጉ የተዘረጋው የሙግት አመራር ሥርዓት በጥብቅ ተግባራት መደረግ ነበረበት፡፡ የስር ፍርድ ቤቶች አንደኛ ተከሳሽ የነበረው ድርጅት ሕጋዊ ሰውነት ያለውና ያልከሰመ መሆን ያለመሆኑን በአግባቡ ሰያጣሩ ጥሪ ቢደረግለትም አይቀርብም በሚል ሰበብ እውነት የማፈላለግ ግዴታቸው (truth finding) ወደ ጎን በመተው ሕጉን የዘረጋው የሙግት አመራር ሥርዓት ሳይከተሉ ከውሳኔ ላይ መደረሳቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት መፈጸማቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ ከላይ እንደተመለከተው ድርጅቱ ጥፋተኛ ሳይባል ስራአስኪያጅ ነበሩ የተባሉ የአሁኑ አመልካች በወንጀል ተጠያቂ ማድረግ በአዋጅ ቁጥር 285 እና 286/1994 የተደነገገው የድርጅት እና ሥራአስኪያጅ የተጠያቂነት አወሳሰን ቅደም ተከተል ያዛባ ሂደት ነው፡፡ በመሆኑም የስር ፍርድ ቤቶች ይሁን አብላጫው ድምጽ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የገቢ አዋጆች ስለ ድርጅት እና ስራአስኪያጅ የወንጀል ተጠያቂነት አወሳሰን ማለትም የድርጅቱ ጥፋተኝነት በቅድሚያ የማረጋገጥ ሕጋዊ ግዴታ ታልፎ አመልካች ጥፋተኛ ናቸው በማለት የሰጡት ውሳኔ የአዋጆች ዓለማና ግብ ያላገነዘበ ነው የሚል እምነት አለኝ፡፡
በሥር ፍርድ ቤት አንደኛ ተከሳሽ የነበረው ድርጅት /ሜጋ ኪነጥበባት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በዚህ አገር በንግድ ህግ ተመዝግቦ የሚሰራ ድርጅት ከነበረ ስለ ድርጅቱ ሕጋዊ ሰውነት ያለው መሆን ያለመሆን ከከሰመም መቼና በማን ውሳኔ የሚሉ ነጥቦች ሊጣሩ የሚገባቸው ነጥቦች ናቸው፡፡ ምክንያቱም አመልካች ድርጅቱ ከመሰከረም 5/2002 ጀምሮ የፈረሰ ስለመሆኑ ሲከራከሩ ተጠሪ በበኩሉ ድርጅቱ አልፈረሰም ተሰውሯል በማለት መልስ አቅርበዋል፡፡ ሕግና ሥርዓት ባለበት አገር አንደኛ ተከሳሽ የነበረው ድርጅት በእርግጥ ሕጋዊ ሰውነት ያለው ህያው ድርጅት ከሆነ ከሚመለከታቸው አካላት በማጣራት እውነት የማፈላላግ ሥራ መከናወን ነበረበት፡፡ በሌላ በኩል ድርጅቱ ሜጋ ማስታወቂያ ከተባለው ድርጅት ከተዋሃዳ የተቀለቀለ / Amalgamation merge /ስለመሆኑ በክርክር ሂደት ተነስቷል፡፡ ይህ በተመለከተም ሁለቱም ድርጅቶች ተዋህደው ከሆነ መቼ እና በማን ውሳኔ ሰሚነት ተዋሀዱ የሚለው መጧራት ነበረበት፡፡ አመልካች እንደሚሉት በክርክር ጊዜ አግባብነት ያላቸው ሰነዶች ለማግኘት እንደተቸገሩ በተለይም ድርጅቱ ህያው ካልሆነ እና የድርጅቱ ሕጋዊ ሠራሽ የሆነው ድርጅት ወይም ግለሰብ በጉዳዩ ጣልቃ በመግባት ካልተከራከሩ ዞሮዞሮ የአመልካች የመከላከል ሕግ መንግስታዊ መብት ማጣበቡ የማይቀር ነው፡፡ የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች በተጠሪ ምስክሮች መሰቀለኛ ጥያቄ በማቅረብ ስለተከራከሩ የተጣበበ መብት የለም በማለት በውሳኔው ያሳፈረ ቢሆንም ክርክሩ ግለሰባዊ ጉዳይ ሳይሆን የአንድ ድርጅት ጥፋተኛ መሆን ያለመሆን ብሎም የድርጅቱ ሥራአስኪያጅ የወንጀል ተጠያቂነት የሚያስከትል ጉዳይ በመሆኑ ድርጅቱ እና የአሁኑ አመልካች ፈጸሙት የተባለው የወንጀል ድርጊት ለመከላከል መቅረብ ያለባቸው ሕጋዊ ሰነዶች እና የክርክር ነጥቦች ከድርጅቱ የተያያዙ አይደለም የሚለው ድምዳሜ የህጉን አጠቃላይ ይዘትና መንፈስ ያላገናዘበ ነው፡፡ ከላይ እንደተመለከተው የሥር ፍርድ ቤት ይሁን ጉዳዩ በይግባኝ የተመለከተው ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሥር ፍርድ ቤት አንደኛ ተከሳሽ የነበረው ድርጅት ህያው ድርጅት ነው ወይስ የከሰመ ድርጅት? የከሰመ ድርጅት ከሆነ መብትና ግዴታው ለማን ተላለፈ? የሚሉትና ተያያዥ ነጥቦች በማጣራት ድርጅቱ ጥፋተኛ ነበር ወይስ አልነበረም? የሚለው በቅድሚያ ውሳኔ መስጠት ይጠበቅባቸው ነበር፡፡
በማጠቃለል በሥር ፍርድ ቤት አንደኛ ተከሳሽ የነበረው ሜጋ ኪነጥበበት ማዕከል ኃ/የተ የግል ማህበር በቅድሚያ በሕጉ አግባብ ጥሪ ተደርጎለት ራሱ ወይም ህልውናው የከሰመ ከሆነ መብትና ግዴታው የወረሰው ድርጅት/ተቋም/ ግለሰብ ሳይጣራ እና በአግባቡ ተጣርቶ ጥፋተኛ ሳይባል አመልካች ጥፋተኛ ናቸው ተብሎ መወሰኑ በአግባቡ አይደለም፡፡ በሥር አንደኛ ተከሳሽ የነበረው ድርጅት ህልውና ካበቃ ወይም መብቱና ግዴታው የተላለፈለት ድርጅት/ግለሰብ ከሌለ በእርግጥ በሥራ አስኪያጅ የወንጀል ተጠያቂነት ያስከትላል ወይ የሚለውም ከወንጀል ቅጣት ዓላማና ግብ መታየት ነበረበት፡፡ ሜጋ ኪነጥበባት ማዕከል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እና ሜጋ ማስታወቂያ ድርጅት በሕጉ አግባብ ያልተዋሀዱ ከሆነ የወንጀል ተጠያቂነት የሚያስከትለው ውህዳቱን የወሰኑ እና ያስፈጸሙ የየድርጅቱ ባለቤቶች ናቸው ወይስ ሥራ አስኪያጅ ነው ተጠያቂ መሆን ያለበት? የሚለውን በአግባቡ የተጣራ ጉዳዩ አይደለም፡፡ በእነዚህ ሁሉ ምክንያቶች የሥር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሊሻር ይገባ ነበር በማለት በሐሳብ ተለይቻለሁ፡፡
የማይነበብ የአንድ ዳኛ ፊርማ አለበት
ሩ/ለ
The Federal Supreme Court has released Cassation decisions volume 17.
Click the link below to download the file.
የዕጩ ዳኞችን ዝርዝር ለማግኘት እዚህ ይጫኑ
ቀን : 26/4/2008
ለህዝብ አስተያየት የተመረጡ እጩ ተወዳዳሪ ዳኞች ስም ዝርዝር ይፋ ሆነ ለከፍተኛ ፍርድ ቤትና ለፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በእጩ ዳኝነት ከተወዳደሩት ውስጥ ለህዝብ አስተያየት የተመረጡ ተወዳዳሪዎች ስም ዝርዝር ይፋ ሆነ፡፡ የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ጽ/ቤት እንደገለፀው በተሰጠው የቃል ፈተና የተሻለ ውጤት ያመጡ ተወዳዳሪዎች ለእጩ ዳኝነት ከመቅረባቸው በፊት ህዝብ አስተያየት እንዲሰጥባቸው የስም ዝርዝራቸው ይፋ ተደርጓል፡፡ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 26 ወንድ እና 13 ሴት በድምሩ 39 እጩ ተወዳዳሪ ዳኞች ለህዝብ አስተያየት የቀረቡ ሲሆን ለፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት 77 ወንድ እና 44 ሴት በድምሩ 121 እጩ ተወዳዳሪ ዳኞች ለህዝብ አስተያት ቀርበዋል፡፡ በዚሁ መሰረት ለሁለቱም ፍርድ ቤቶች የተመረጡ እጩ ተወዳዳሪ ዳኞች ስም ዝርዝር በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ድረ ገጽ /www.fsc.gov.et/ እና ፌስቡክ ገጽ /www.facebook.com/The Federal Supreme Court of Ethiopia/ ላይ ይፋ የተደረገ ሲሆን ከታህሳስ 25 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ ባሉ ተከታታይ 10 (አስር) ቀናት ውስጥ ማንኛውም ሰው በእጩ ተወዳዳሪ ዳኞቹ ላይ ያለውን አስተያየት መስጠት የሚችል መሆኑ ተገልጿል፡፡ የህዝብ አስተያየት ተወዳዳሪ እጩ ዳኞችን በመመልመል ሂደት ውስጥ የመጨረሻው መሆኑን የገለጸው የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ጽ/ቤት በእጩ ተወዳዳሪ ዳኞች ላይ አስተያት መስጠት የሚፈልጉ አካላት በጉባኤው ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011 1 565687 በመደወል ወይም በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ድረ-ገጽ ላይ የተዘጋጀውን ቅጽ ተጠቅመው አስተያታቸውን እንዲሰጡ ጠይቋል፡፡ ይህም የተወዳዳሪ እጩ ዳኞችን የሙያ ብቃት፣ ስነምግባር፣ ህግ አክባሪነት፣ አመለካከት እና ባህሪ እንዲሁም በህዝብ ያላቸው ተቀባይነትን ለመረዳት በማስፈለጉ ነው፡፡ የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ሕዳር 18 እና 19 / 2ዐዐ8 ዓ.ም. የፅሁፍ ፈተናውን ላለፉ በአጠቃላይ 172 እጩ ተወዳዳሪ ዳኞችና 22 ረዳት ዳኞች የቃል ፈተናውን በጉባዔው አባላት አማካይነት መሰጠቱ ይታወሳል፡፡
The Federal Supreme Court has released Cassation decisions volume 18.
Click the link below to download the file.
በ2008 ዓ.ም. ለፍሬ ለማብቃት ካቀድኳቸው ሥራዎች ውስጥ ሁለቱ ተጠናቀው አንደኛው ደግሞ ተገባዶ በማየቴ በተለምዶ ‘እጥፍ ድርብ’ የሚባለው ዓይነት ባይሆንም ትልቅ ደስታና እፎይታ ተሰምቶኛል፡፡ ይንንም ለ Ethiopian Legal Brief ጎብኚዎች በተለይም ደግሞ ለድረ ገጹ ቋሚ ተከታታዮች (followers and subscribers) ለማጋራት በማሰብ ብሎም ቅድመ ህትመት ለአንባቢ መተዋወቂያ ይሆን ዘንድ የአንደኛውን ሥራ የይዘት ማውጫ፤ የውሳኔዎች ማውጫ፤ የህግጋት ማውጫ፤ ዋቢ መጻህፍትና የቃላት ማውጫ ከቅንጭብ ጽሑፎች (የተመረጡ ገጾች) ጋር በዚህ ገጽ ላይ ለማቅረብ እወዳለው፡፡
በመጀመሪያ የሶስቱም ያልታተሙ ሥራዎች ርዕስና ገጽ ብዛት እነሆ!
አሠሪና ሠራተኛ ህግ፡ የሰበር ችሎት እንደተረጎመው
በዚህ ሥራ ከ1998 እስከ 2007 ዓ.ም. ድረስ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የህግ ትርጉም የሰጠባቸው የታተሙ (ቅጽ 1 እስከ 18) እንዲሁም ያልታተሙ በጠቅላላይ ከ240 በላይ በሚሆኑ የሰበር ውሳኔዎች ላይ ዳሰሳ ተደርጓል፡፡ ልክ የዛሬ ዓመት የካቲት 2007 ዓ.ም. ላይ ሥራው ሲጀመር ከይዘት አንጻር ዋነኛ ትኩረት የተደረገው ገላጭ የሆነ ዘዬ በመከተል የሰበር ችሎት ትርጉም የሰጠባቸውን ጉዳዮች በየፈርጁና በየርዕሱ በመለየት የህጉን ይዘት በጥልቀት መፈተሸ ነበር፡፡ ሆኖም ‘የሌሎች አገራት ልምድ’ እንዲካተት ተደጋጋሚ አስተያየት በመቅረቡ ባደጉትና ባላደጉት አገራት የአሠሪና ሠራተኛ ህግ ይዘቱና አፈጻጸሙ በከፊል ተቃኝቷል፡፡
በመጽሐፉ ውስጥ የተጠቀሱ ህግጋትና የሰበር ውሳኔዎች በቀላሉ ማግኘት እንዲቻል የውሳኔዎች ማውጫ (Table of Cases) እና የህግጋት ማውጫ (Table of Legislations) ለብቻው ተዘጋጅቷል፡፡ የቃላት ማውጫው (Index) የቃላት ሳይሆን የተዛማጅ ርዕሰ ጉዳዮች መጠቆሚያ እንዲሆን ጥረት ተደርጓል፡፡
ማውጫዎቹንና የተመረጡ ጽሑፎችን ለማውረድና ለማንበብ DOWNLOAD የሚለውን link ተጫኑት፡፡
ማውጫ DOWNLOAD
የሰበር ውሳኔዎች ማውጫ DOWNLOAD
የሕግጋት ማውጫ DOWNLOAD
ዋቢ መጻህፍትና ጽሑፎች DOWNLOAD
የቃላት ማውጫ DOWNLOAD
የተመረጡ ገጾች
ዝውውር እና የአሠሪው ስልጣን፡ የሰበር አቋም ሲፈተሽ DOWNLOAD
የኃይማኖት ተቋም ሠራተኞች DOWNLOAD
በጥፋት ምክንያት ሠራተኛን ስለማሰናበት DOWNLOAD
የሥራ መደብ መሰረዝ DOWNLOAD
ረቂቅ አዋጆቹ በመስጠት ለተባበረኝ ብሎም የአሠሪና ሠራተኛ መጽሐፍ ረቂቁን አንብቦ ጠቃሚ ሂስ እና አስተያየት ለሰጠኝ ለጠበቃ ወረደ ኃይሉ (ድሬዳዋ) በዚህ አጋጣሚ ምስጋናዬን እገልጻለው፡፡