Quantcast
Channel: Ethiopian Legal Brief
Viewing all articles
Browse latest Browse all 992

ለህዝብ አስተያየት የተመረጡ እጩ ተወዳዳሪ ዳኞች ስም ዝርዝር ይፋ ሆነ

$
0
0

የዕጩ ዳኞችን ዝርዝር ለማግኘት እዚህ ይጫኑ

ቀን : 26/4/2008

ለህዝብ አስተያየት የተመረጡ እጩ ተወዳዳሪ ዳኞች ስም ዝርዝር ይፋ ሆነ ለከፍተኛ ፍርድ ቤትና ለፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በእጩ ዳኝነት ከተወዳደሩት ውስጥ ለህዝብ አስተያየት የተመረጡ ተወዳዳሪዎች ስም ዝርዝር ይፋ ሆነ፡፡ የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ጽ/ቤት እንደገለፀው በተሰጠው የቃል ፈተና የተሻለ ውጤት ያመጡ ተወዳዳሪዎች ለእጩ ዳኝነት ከመቅረባቸው በፊት ህዝብ አስተያየት እንዲሰጥባቸው የስም ዝርዝራቸው ይፋ ተደርጓል፡፡ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 26 ወንድ እና 13 ሴት በድምሩ 39 እጩ ተወዳዳሪ ዳኞች ለህዝብ አስተያየት የቀረቡ ሲሆን ለፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት 77 ወንድ እና 44 ሴት በድምሩ 121 እጩ ተወዳዳሪ ዳኞች ለህዝብ አስተያት ቀርበዋል፡፡ በዚሁ መሰረት ለሁለቱም ፍርድ ቤቶች የተመረጡ እጩ ተወዳዳሪ ዳኞች ስም ዝርዝር በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ድረ ገጽ /www.fsc.gov.et/ እና ፌስቡክ ገጽ /www.facebook.com/The Federal Supreme Court of Ethiopia/ ላይ ይፋ የተደረገ ሲሆን ከታህሳስ 25 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ ባሉ ተከታታይ 10 (አስር) ቀናት ውስጥ ማንኛውም ሰው በእጩ ተወዳዳሪ ዳኞቹ ላይ ያለውን አስተያየት መስጠት የሚችል መሆኑ ተገልጿል፡፡ የህዝብ አስተያየት ተወዳዳሪ እጩ ዳኞችን በመመልመል ሂደት ውስጥ የመጨረሻው መሆኑን የገለጸው የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ጽ/ቤት በእጩ ተወዳዳሪ ዳኞች ላይ አስተያት መስጠት የሚፈልጉ አካላት በጉባኤው ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011 1 565687 በመደወል ወይም በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ድረ-ገጽ ላይ የተዘጋጀውን ቅጽ ተጠቅመው አስተያታቸውን እንዲሰጡ ጠይቋል፡፡ ይህም የተወዳዳሪ እጩ ዳኞችን የሙያ ብቃት፣ ስነምግባር፣ ህግ አክባሪነት፣ አመለካከት እና ባህሪ እንዲሁም በህዝብ ያላቸው ተቀባይነትን ለመረዳት በማስፈለጉ ነው፡፡ የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ሕዳር 18 እና 19 / 2ዐዐ8 ዓ.ም. የፅሁፍ ፈተናውን ላለፉ በአጠቃላይ 172 እጩ ተወዳዳሪ ዳኞችና 22 ረዳት ዳኞች የቃል ፈተናውን በጉባዔው አባላት አማካይነት መሰጠቱ ይታወሳል፡፡


Filed under: Uncategorized

Viewing all articles
Browse latest Browse all 992

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>